🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፦በኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የተመራ ከፍተኛ የመንግሥት ልዑክ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ጉባኤ (AIM Congress) ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ማምሻውን ዱባይ ገብቷል።
በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የተመራው ልዑክ ዱባይ ሲደርስ በአገሪቷ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው የኢዜአ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘግቧል።
የኢንቨስትመንት ጉባኤው ከነገ ጳጉሜን 2 እስከ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት በዱባይ ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል ይካሄዳል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 የተቋቋመው ይህ የኢንቨስትመንት ጉባዔ ውጤታማ የኢንቨስትመንት የማስተዋወቂያ ስትራቴጂዎችን በማሳደግና ለኢኮኖሚ ምርታማነት እድሎችን በማመቻቸት የዓለምን ኢኮኖሚ ለማጎልበት የሚሰራ የኤም ግሎባል ፋውንዴሽን ኢንሼቲቭ ነው።

በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስፋት፣ በአገራት መካከል አጋርነትና የኢኮኖሚ ትብብርን በማጠናከር እንዲሁም በመስኩ የሚስተዋሉ ችግሮችን እልባት በመስጠት በመካከለኛው ምስራቅ ዋነኛ የኢንቨስትመንት መድረክም ሆኖ እያገለገለ ነው።
በጉባኤው የአገራት መሪዎች፣ በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ግዙፍ የቢዝነስና ተቋማት ሥራ አስፈጻሚዎች፣ፖሊሲ አውጪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ የከፍተኛ ትምህርትና የምርምር ተቋማት ተወካዮች፣ሌሎች የዘርፉ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በመድረኩ በጋራ ይመክሩበታል።
በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ዘንድሮ ለ15ኛ ጊዜ በሚካሄደው በዚሁ የዱባይ ጉባኤ ታዳሚዎች በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በዘላቂ ልማትና በስትራቴጂያዊ አጋርነት ላይ ትኩረት አድርገው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህንንም ተከትሎ መድረኩ የዓለምን ኢኮኖሚ ለማጠናከር የሚያስችሉ ውጤታማ ውይይቶችና ግዙፍ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች እንደሚያደረጉ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል።
ኢትዮጵያ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በተለይም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን በመሣብና የኢኮኖሚ ትብብሮችን በማጠናከር የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ለማሣደግና ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ እየሠራች ነው።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026