🔇Unmute
ጅግጅጋ፣ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦በጅግጅጋ ከተማ እየተከናወኑ በሚገኙ የልማት ሥራዎች የሥራ ዕድል እየተፈጠረላቸው መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ እንደገለፁት፤ በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ምቹ የመኖሪያ ከባቢን ከመፍጠር ባለፈ የሥራ ዕድል እየፈጠሩ ናቸው።
ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ዩሱፍ ሀሰን በሰጡት አስተያየት፤በከተማዋ በኮሪደር ልማት የተገነቡ መንገዶች የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በእጅጉ እያሳለጡ ይገኛሉ።
ይህም ቀደም ሲል ይታይ የነበረውን የእግረኛ እና የተሽከርካሪ መጨናነቅ በመፍታት፣ ይባክን የነበረውን ጊዜና ጉልበት መቆጠብ ማስቻሉን ጠቁመዋል።
አክለውም የልማት ሥራዎቹ የከተማዋን ውበት ከማጉላት ባለፈ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ተጨማሪ አቅም መሆናቸውን አስረድተዋል።

ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ ወጣት ከድር አብዲ በበኩሉ፤ በከተማዋ የተገነቡ መናፈሻዎችና ፓርኮች፣ እንዲሁም በኮሪደር ልማት በመንገዶች ዳር የተተከሉ አረንጓዴ ዛፎች ለጅግጅጋ ልዩ ውበት ማበርከታቸውን ተናግረዋል።
በተለይም የተሠሩት አዳዲስ የእግረኛ መንገዶች ነዋሪው በእግር ተጉዞ ለመዝናናትና ጤናውን ለመጠበቅ አጋዥ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የከተማዋ ፈጣን ልማት ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድ ለወጣቶች የሥራ ዕድልን ለማስፋት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን መረዳቱንም አክሏል።

አቶ ዘመቻ ይርጋ የተባሉ ነዋሪም ጅግጅጋ በከፍተኛ የለውጥ ምዕራፍ ላይ መሆኗን ጠቅሰው፣ የተከናወኑት ሥራዎች የነዋሪውን የመሠረተ ልማት እና የመንግሥት አገልግሎቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሳለጡ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።
የከተማዋን ዕድገት ለማፋጠን በሚደረገው ሁለንተናዊ ተሳትፎም የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጅግጅጋ ከተማ ዘመናዊ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ለከተማዋ አዲስ ምዕራፍ የከፈቱ ናቸው ያሉት ደግሞ አቶ ኢብራሂም አብዲ አሊ ናቸው።
በተለይም የኮሪደር ልማት በተከናወነባቸው መንገዶች ላይ ከተማዋ ልዩ ድምቀትና አዲስ ውብ ገጽታ መላበሷን አስረድተዋል።
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...
Oct 20, 2026
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026