የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የክልሉን ሀብቶች ለይቶ በማልማት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ወደ ተግባር ተገብቷል

Oct 22, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ቡታጅራ ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦ በክልሉ ያሉ ሀብቶችን ለይቶ በማልማት እና የህዝብን አብሮነት በማጠናከር ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ወደ ተግባር መገባቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ገለፁ።

"በመደመር መንግስት፣ የሕዝብ ድምፅ፣ የጋራ ተሳትፎ፣ የጋራ ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ህዝባዊ የምክክር መድረክ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው።


ርዕሰ መስተዳድሩ በምክክር መድረኩ ላይ እንዳሉት የመደመር መንግስት የህዝቡን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ውጥን ይዞ ወደ ተግባር ገብቷል።

ለእዚህም በክልሉ ያሉትን ሀብቶች ለይቶ በማልማትና የህዝብን አብሮነት በማጠናከር የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በክልሉ ሰላምና ልማትን በዘላቂነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ አሰራር ጋር በማቀናጀት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

በክልሉ ያሉ የልማት ፀጋዎች ለይቶ ከማልማት በተጨማሪ የህዝቡን አብሮነት በማጎልበት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ተግባራዊ ሥራ መጀመሩንም አስታውቀዋል።


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በክልሉ የመደመር መንግስት እሳቤን ተግባራዊ በማድረግ የህዝቦችን አብሮነት ለማሳደግ እና ልማትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን እየተሰራ ነው።

ለዚህም የማህበረሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማዕከል ያደረገ አሰራር መዘርጋቱንና ቴክኖሎጂን እውን ማድረግ መጀመሩን አንስተው፣ የምክክር መድረኩም ይህን ለማስቀጠል ያለመ ነው ብለዋል።


የምስራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሱ አበጋዝ በበኩላቸው ፤ በዞኑ በግብርናው ዘርፍ ያሉ እድሎችንና ሌሎች የልማት አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ጠቁመዋል።

በዞኑ ፈጣን ልማት በማረጋገጥ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎችን ለማስቀጠል የምክክር መድረኩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የማህበረሰብ ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026