🔇Unmute
ባህርዳር፣ ጥቅምት 19/2019(ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር በምግብ ራስን ለመቻል እየተደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ የሚደርስ ጉዳትን በራስ አቅም ለመቋቋም በተሰራው ስራ በመኸር የምርት ዘመን ከ235 ሺህ ኩንታል በላይ የመጠባበቂያ ምርት እየተሰበሰበ መሆኑም ተገልጿል።
ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባታብል ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገር በምግብ ራስን ለመቻል እየተደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ ነው።
በመኸር ምርት ዘመኑ በቆሎና ስንዴን ጨምሮ በሌሎች ሰብሎች ከለማው መሬት ከ235 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እየተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም በሂደት ከውጭ እርዳታ ጥገኝነት በመላቀቅ "በራሳችን አቅም ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ፈጥነን ለመድረስ የሚያስችል ውጤታማ ተግባር ነው" ብለዋል።
የክልሉ መንግስት በመደበው 800 ሚሊዮን ብር የምግብ እህል በመግዛት ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እየተሰራጨ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በተጨማሪም ከተቋማት፣ ከባለሃብቱና ከህብረተሰቡ እስካሁን ከ650 ሚሊዮን ብር በላይ በማሰባሰብ እህል በመግዛት ለችግር ለተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ፈጥኖ ለመድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በፌደራል መንግስት ኢኒሼቲቭ ተቀርጾ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በመኸር ምርት ዘመኑ በኢኒሼቲቭ የተዘራውን ሰብል ከብክነትና ከብልሽት በጸዳ መልኩ በመሰብሰብ ለተገቢው ዓላማ ለማዋል እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በተጨማሪም የክልሉ መንግስት ተገቢውን በጀት በመመደብ የመጠባባቂያ እህል ክምችትን ለማሳደግ ትኩረት ማድረጉን ገልጸዋል።
ህብረተሰቡም የመረዳዳት ባህሉን በመጠቀም ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለመድረስ እያሳየ ያለው ተግባር የሚበረታታ መሆኑንም አመልክተዋል።
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...
Oct 20, 2026
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026