የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ ይለማል

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦በሰሜን ሸዋ ዞን ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ እንደሚለማ የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።

የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ የ2019 የበጋ መስኖ የንቅናቄ መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ አካሂዷል።


የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ ዓለማየሁ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ የበጋ መስኖ ልማት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

በዘንድሮው በጋ ለሚካሄደው የመስኖ ልማትም አርሶ አደሩን በማንቃት፣ ግብዓትን በወቅቱ በማቅረብና አዳዲስ አሠራሮችን በመተግበር ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተያዘው ዓመትም በዞኑ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት ዕቅድ ተይዞ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ማሙሻ በበኩላቸው፣ በበጋ መስኖ የሚለማው ስንዴ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ለምግብ ብቻ ሳይሆን ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት እንደሚውል ተናግረዋል።


የዛሬው የንቅናቄ መድረክም የተጀመሩ የመስኖ ልማት ሥራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል የታቀደውን ለማሳካት ያለመ መሆኑንም አመልክተዋል።

በመስኖ ከሚለማው 76 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥም 60 ሺህ ሄክታሩን በኩታ ገጠም ስንዴ በማልማት 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት መታቀዱን አስታውቀዋል።


የቀወት ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት የመስኖ መሐንዲስ አቶ ታምሩ አሽኔ፣ የገጽና ከርሰ ምድር ውሃን በመጠቀም 4 ሺህ 438 ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

እስካሁን በተደረገ ጥረትም 837 ሄክታር መሬት በበጋ ስንዴ ዘር መሸፈኑን አስረድተዋል።


በአጎለላና ጠራ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት የመስኖ መሐንዲስ አቶ በላይነሀ ሲገኝ በበኩላቸው፣ በወረዳው በኩታ ገጠም ስንዴን በመስኖ የማልማት ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026