🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦የአዲስ አበባ ከተማ አስደናቂ ክትመትና የመሰረተ ልማት ዕድገት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አርዓያ ይሆናል ሲሉ የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ልዑካን ቡድን አባላት ገለጹ።
ከጥቅምት 18 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤቶች የልምድ ልውውጥ መድረክ ተጠናቋል።

የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት ልዑካን ቡድን አባላት ከልምድ ልውውጡ ባሻገር በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በመዲናዋ ባለው ፈጣን የመሰረተ ልማትና የከተሜነት ዕድገት እንዲሁም በሳቢነቷ ተደንቀዋል።
የልዑካን ቡድኑ አባል ዶርካስ ዳዊዶ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለጎብኝዎች ደግሞ አስደማሚ ነው።

በሁሉን አቀፍ መሰረተ ልማትና በአረንጓዴ ሥፍራዎች ያጌጠች መሆኗን ገልጸው፤ ታንዛኒያ የኢትዮጵያ የልማት ተሞክሮ እንድትወስድ የድርሻዬን እወጣለሁ ብለዋል።
የታንዛኒያ የካፒታል ገበያ ፍርድ ቤት የሕግ ባለሙያ ኤልያድ ኢ-መንደም፤ የከተማዋን ፈጣን ዕድገትና የኢትዮጵያውያንን ታሪካዊ አርበኝነት የሚያስደንቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በእግር ጉዞ የተለያዩ አካባቢዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸው፤ የመዲናዋ መሠረተ ልማት፣ የመንገዶችና የሕንፃዎች ግንባታ በማራኪ ሁኔታ ተለውጧል ብለዋል።
አንድነት ፓርክንና የዓድዋ ድል መታሰቢያን በጎበኙበት ወቅት ያዩት የኢትዮጵያውያን ጽናት እና ቁርጠኝነት ለአፍሪካውያን ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጥ አንስተዋል።
የታንዛኒያ ፋይናንስ ሚኒስቴር የዕቅድ መምሪያ ኃላፊ ኤልያስ ሬይመንድ ማፑንዳ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በከተማ ዕቅድና በልማት ዘርፍ ያሳየችው ስኬት ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ ትምህርት ይሆናል ብለዋል።

የታንዛኒያ መንግሥት ከኢትዮጵያ የልማትና የቢዝነስ እንቅስቃሴዎች በርካታ ልምዶች መቅሰም እንደሚችል ገልጸዋል።
ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ያሳዩትና አሁንም የሚያንፀባርቁት አንድነት ለሀገር ዕድገትና ልማት መሰረት መሆኑን ገልጸው፤ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ ፤ታላቅ ርዕይ
#የመደመር_መንግሥት
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...
Oct 20, 2026
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026