የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የመስኖ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያገዘ ነው -ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሰመራ፤ ጥቅምት 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በአፋር ክልል የመስኖ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያገዘ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በክልሉ ገቢ ረሱ ዞን በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በክልሉ የመስኖ ልማት ስራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያገዘ ነው።

በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ እየተካሄደ ያለው የመስኖ ልማት ስራም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።


በወረዳው በ100 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ ያለው ጤፍ ጥሩ ጅማሮ መሆኑን ጠቁመው በተመሳሳይ በ150 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ ያለው በቆሎም በመልካም ተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል። የመስኖ ልማቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አደን በልአ በበኩላቸው እንዳሉት፤ በወረዳው ዘንድሮ በበጋ መስኖ 9 ሺህ 200 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ ሰብሎች እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬ ለማልማት ታቅዶ ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

እስካሁን ባለው ሂደት 4 ሺ 500 ሄክታር መሬት መልማቱን ተናግረዋል።


የበጋ መስኖ ልማት አርብቶ አደሩን ከእንስሳት እርባታ በተጓዳኝ በግብርና ስራ በመሰማራት ተጠቃሚ እያደረገው መሆኑን አመልክተዋል።

የወረዳው አርብቶ አደሮች በመስኖ በመታገዝ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም እንዲሁም ሀብሀብና ሙዝ በሰፊው በማምረት ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን አስታውቀዋል።

በመስክ ምልከታው የክልሉ፣ የዞንና የወረዳ የስራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026