የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

አዲስ አበባ ለኑሮ፣ ለቱሪዝም እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ሆናለች

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማት በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት እየተገነባ በመሆኑ፣ መዲናዋን ለኑሮ፣ ለቱሪዝም እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ አድርጓታል ሲሉ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ገለጹ።

ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ የወንዝ ዳርቻ ልማቱ የከተማዋን ውበት በማሳደግ፣ ለነዋሪዎች የመዝናኛ እና የማኅበራዊ ትስስር ለማጠናከር እንዲሁም ለቱሪዝም ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል።


ከሐረር የመጣችው ወጣት ስጦታ ታሪኩ፣ በአዲስ አበባ የተሠሩት የልማት ሥራዎች እጅግ የሚያምሩና ለጎብኚዎች ሳቢ መሆናቸውን ተናግራለች።

በተለይም ለወጣቶች አእምሮን የሚያድሱበት፣ ከዕለት ተዕለት ጫና ዘና የሚሉበትና ጊዜያቸውን በጥራት የሚያሳልፉባቸው ምቹ ሥፍራዎች ተመልክቻለሁ ብላለች።

እነዚህ የልማት ሥራዎች ለሀገሪቱ የቱሪዝም ፍሰት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተናግራለች።


አቶ ፍቃዱ ቶላ በበኩላቸው፣ ቀደም ሲል የከተማዋ ገጽታ ከንጽህና ጉድለትና ከመጥፎ ሽታ ጋር የተያያዙ ችግሮች የሚታዩባት እንደነበር አስታውሰዋል።

አሁን ግን ከተማዋ በንጽህና፣ በውበትና በአጠቃላይ ገጽታዋ ረገድ ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቷን ገልጸዋል።

በተለይም ነዋሪዎች በቀንም ሆነ በማታ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ወጥተው የሚዝናኑባትና ጥሩ ጊዜ የሚያሳልፉባት ምቹ ከተማ እየሆነች መምጣቷን አክለዋል።

ከተማዋ ከአረንጓዴ ልማት ጋር ተቀናጅታ መገንባቷ የሚያስደስት መሆኑንና ለኑሮ ምቹ እንድትሆን አስተዋጽኦ ማበርከቱን የገለፀችው ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ በጸሎት ሸጋው ናት።


በከተማዋ የተፈጠሩት አረንጓዴ ሥፍራዎችና የመዝናኛ ቦታዎች ዜጎች መጻሕፍትን ለማንበብ፣ ከራሳቸው ጋር ጊዜ ለማሳለፍ፣ ለማሰላሰልና ከዕለታዊ የሕይወት ጫና ለማረፍ የተለያዩ አማራጮችን እንዲያገኙ ማስቻላቸውንም አብራርታለች።

አቶ ዘካሪያስ ተሾመ ቀደም ሲል ከተማ የማስዋብና የመሰረተ ልማቶችን የማሻሻል ሥራ ባለመከናወኑ በርካታ አካባቢዎች ለሕዝብ እንቅስቃሴና ለአገልግሎት ዝግ ሆነው ቆይተዋል ብለዋል።

አሁን ላይ ግን በኮሪደር እና በወንዝ ዳርቻ ልማት የተቀናጁና ፈጣን ሥራዎች በመከናወናቸው አካባቢዎች ንጹሕ፣ ማራኪና ለሕዝብ ክፍት እንዲሆኑ መደረጋቸውን ተናግረዋል።


ይህም ከተማዋ ለነዋሪዎቿ ጤናማና ምቹ የመኖሪያና የመዝናኛ ከባቢ እንድትሆን ማስቻሉን አብራርተዋል።

አቶ አሻግሬ ከሲሳ በበኩላቸው ከተማዋ በተዋበችና የመሰረተ ልማት ዝግጅቷ በጨመረ ቁጥር የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን ትኩረት እንደሚስብ ተናግረዋል።


ይህም ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥርና የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026