የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ሁለንተናዊ የልማት ስኬቶች የሚደነቁ ናቸው  

Nov 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የልማት፣ የዲጂታላይዜሽን እና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስኬቶች ለአፍሪካ ዘላቂ ብልፅግና አርዓያ የሚሆኑና የሚደነቁ መሆናቸውን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ እንግዶች ገለጹ።

"ዕድገትን መምራት፤ ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ ኢኮኖሚ መሃንዲሶች" በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየውን ሁለተኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ትናንት ተጠናቋል።

በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችና የተመዘገቡ ውጤቶችን ጎብኝተዋል።

ተሳታፊዎቹ ለኢዜአ እንዳሉት በኢትዮጵያ በመሠረተ ልማት፣ በከተማ ጽዳትና አረንጓዴ ልማት፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የሚታዩ ለውጦች የሚደነቁ ናቸው።

እንዲሁም በወጣቶች አቅም ግንባታ የተመዘገቡ ስኬቶች ለአፍሪካ ትልቅ ትምህርት የሚሰጡ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል የኬንያ ተመራማሪ ማርቲን ቡሩ እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራቸው ልማት ጉዳይ በጋራ መስራታቸው አርዓያ የሚሆን ነው።

በኢትዮጵያ በከተሞች ውበት፣ በመንገድ መሰረተ ልማት እና በግድብ ግንባታ ዘርፎች የታዩት ለውጦች የሚያስደምሙ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ አህጉራዊ ውህደትን ለማጠናከር የምታደርገው ጥረት ከፍተኛ መሆኑን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

ከኡጋንዳ የመጡት የፓርላማ አባል ኛካቶ አሲናንሲ ካማንዳ በበኩላቸው፤ አዲስ አበባ እጅግ ጽዱ፣ የለማችና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም በአረንጓዴ ልማት የተሸፈነች ውብ ከተማ መሆኗን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ፈጣን ሽግግር እያደረገ መሆኑ አፍሪካውያን በራሳቸው አቅም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን እውን ማድረግ እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

አፍሪካውያን ከውጭ ብድር እና እርዳታ ጥገኝነት ወጥተው በጋራ ሀብታቸውን ማልማት እንዳለባቸው የመከሩት የፓርላማ አባሏ፤ የኢትዮጵያ እና የኡጋንዳ ህዝቦች በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ያላትን የበለፀገ ባህላዊ ሀብት እና እንግዳ ተቀባይነት ለኢኮኖሚ እድገት በብቃት መጠቀም በመቻሏ አድናቆታቸውን የገለፁት ደግሞ የናይጄሪያው የመረጃ ተንታኝ ፋሩክ አዲሳፌ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወጣቶች በፖለቲካውና በልማቱ ምህዳር ውስጥ የላቀ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረጋቸው አርዓያነት ያለው ስራ መሆኑን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉ ሁለንተናዊ የልማት ምዕራፎች፣ የሰላም እና የአንድነት ጉዞዎች ለመላው አህጉሪቱ ብልፅግና ተስፋ ሰጪ ማሳያዎች መሆናቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026