የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የኢትዮ-ኮደርስ ሥልጠና ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለአገልግሎት ቅልጥፍና አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው

Nov 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀረር፤ ጥቅምት 30/2019 (ኢዜአ)፡- የአምስት ሚሊዮን የኢትዮ-ኮደርስ ሥልጠና የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት በማዳበር ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለአገልግሎት መቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋጽአ እያበረከተ መሆኑ ተገለጸ።

ዘርፉን በእውቀት ለመምራት የአሰራርና የፖሊሲ ማዕቀፎች ተቀርጸውለት ወደ ተግባር በመገባቱ ውጤት እየተመዘገበበት እንደሚገኝም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በጉዳዩ ላይ በሐረሪ ክልል ስልጠናውን የወሰዱ የህብረተሰብ ክፍሎችና የሥራ ኃላፊዎችን አነጋግሯል።

የሐረር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የባዮሎጂ መምህር አንባዬ ፍቅሬ እንደገለጹት፤ በኢትዮ-ኮደርስ ሥልጠና ያገኙት ክህሎት ሥራቸውን ወቅቱ በደረሰበት ቴክኖሎጂ በመጠቀም ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ አስችሏቸዋል።

በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በመጠቀም የመማር ማስተማር ሥራቸውን ለማከናወን ከፍተኛ እገዛ እንዳደረገላቸው አንስተዋል።


ሥልጠናው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እውቀቱን ለማዳበር እንደረዳው የገለጸው ደግሞ ወጣት ዮሴፍ አብዱረሃማን ነው።

ሥልጠናው የንድፈ-ሐሳብ እውቀቱን በተግባር የሚያውልበትን ክህሎት ለማዳበርና በሥራ ገበያው ላይ ያለውን ተወዳዳሪነት ለመጨመር እንደጠቀመው አስረድቷል።


የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሱመያ አማን በበኩሏ፥ የኢትዮ-ኮደርስ ሥልጠና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎቷን በማሳደግ በትምህርቷ ውጤታማ የምትሆንባቸውን መረጃዎች ይበልጥ የምትጠቀምበትን ዕድል እንደፈጠረላት ጠቁማለች።

በመሆኑም ሌሎች ወጣቶችና ተማሪዎች ዕድሉን እንዲጠቀሙበት ከልምዷ በመነሳት መክራለች።

የሐረሪ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም በበኩላቸው፤ በክልሉ የ5-ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና የወጣቶችን የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግና የሥራ ፈጠራ ዕድሎችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ አቅም እየሆነ ነው ብለዋል።


ለዚህም ማሳያ በክልሉ ሥልጠናውን በአግባቡ ካጠናቀቁ ከ55 ሺህ በላይ ዜጎች ውስጥ ከ41 ሺህ በላይ የሚሆኑት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው የምስክር ወረቀት ማግኘት መቻላቸውን አመልክተዋል።

በክልሉ ያሉ ወጣቶች ሥልጠናውን ወስደው በቀጥታ ወደ ሥራ እንዲገቡ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል።

ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል በበጀት ዓመቱ 20 ሺህ የሚሆኑ አዳዲስ ወጣቶችን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ መተግበሪያ ማበልጸግ (Android Development)፣ በዳታ ሳይንስና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ ለማድረግ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል።

ኢትዮ-ኮደርስ ሥልጠና በክልሉ የመንግሥት አገልግሎትን ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተደራሽ ለማድረግ ጭምር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አክለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026