🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 8/2019(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በ2026ቱ የክላይሜት ስካነር የላቀ ተፅዕኖ ሽልማት አመርቂ ውጤት በማምጣት ተሸላሚ ሆነ።
የኢትዮጵያ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት (OFAG) በ2026ቱ የክላይሜት ስካነር የላቀ ተፅዕኖ ሽልማት (ClimateScanner Impact Awards 2026) በምድብ 3 «ለተቋማዊ አሠራር መጎልበት ያለ ቁርጠኝነት» ዘርፍ አሸናፊ ሆኗል።

ይህም የመደመር መንግሥት በአየር ንብረት አጠባበቅና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ያከናወናቸውን ውጤታማ ሥራዎች የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በኦዲት ሥራው መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና በማስረጃ በማስደገፍ የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ በመቻሉ መሆኑም ተመላክቷል።
የዚህ ስኬት መነሻም እ.ኤ.አ. ከጁላይ 24 እስከ 26 ቀን 2024 በሩሲያ ፌዴሬሽን አካውንትስ ቻምበር አዘጋጅነት በኡፋ ከተማ በተካሄደው 4ኛው የብሪክስ አገራት ዋና ኦዲተሮች ጉባኤ ላይ የተደረሰው ስምምነት መሆኑም ተጠቅሷል።
በጉባኤውም የተሳተፉት ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ፣ ከመድረኩ ጎን ለጎን የወቅቱ የአየር ንብረት አስተባባሪ ከነበሩት የብራዚል ዋና ኦዲተር ጋር በመወያየት የመጀመሪያውን የአየር ንብረት አጠባበቅ ኢኒሼቲቭ ሰነድ ተቀብለው ተግባራዊ ለማድረግ መስማማታቸው እንዲሁ።
በስምምነቱ መሠረትም ቡድን በማደራጀት፣ በመምራትና በማስተባበር ግምገማው በሀገራችን እንዲካሄድ በማድረጋቸው ውጤቱ ሊመዘገብ መቻሉም ተጠቅሷል።
ሽልማቱ ከተለያዩ ሀገራት የዋና ኦዲት ተቋማትና አጋር አካላት በተውጣጣ ዓለም አቀፍ የዳኞች ቡድን የተመረጠ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፤ እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 5 እና 6 ቀን 2026 በብራዚል ሪዮ ዴ ጄኔሮ በተካሄደው የ2026ቱ የክላይሜት ስካነር ጉባኤ ልዩ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ ይፋ መደረጉ ተገልጿል።
በተለይም የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለምድብ 3 እውቅና በሚያበቁ ተግባራት ረገድ ዘላቂ ተቋማዊ አሠራር በመዘርጋቱ እውቅናው እንደተሰጠውም ተመላክቷል።
መሥሪያ ቤቱ ራሱን የቻለ የአካባቢ ክዋኔ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ያቋቋመ ሲሆን፣ ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የሚሰጥ ኦዲትንም በስትራቴጂክ ዕቅዱ (እ.ኤ.አ. 2026–2031) ውስጥ የተካተተ መሆኑም ተጠቅሷል።
በተጨማሪም የዘላቂ ልማት ግቦች (SDG) የክዋኔ ኦዲት ማኑዋልን (2026) በሥራ ላይ በማዋል የመደመር መንግሥት በአየር ንብረት አጠባበቅና የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ያከናወናቸው ውጤታማ ሥራዎችና የመጡ ለውጦች በየጊዜው ኦዲት ተደርገው እንዲታዩ አድርጓል ተብሏል።
ከዚህም ጋር እንደ ቲምሜት ፕላስ (TeamMate+) እና የኦዲት ምክረ ሀሳቦች መከታተያ ሥርዓትያሉ ዲጂታል መሣሪያዎችን በሥራ ላይ ማዋሉም ተገልጿል።
የብራዚል የፌዴራል የኦዲት ተቋም ፕሬዝዳንት እና የክላይሜት ስካነር ኢኒሼቲቭ አስተባባሪ በሆኑት ሚኒስትር ቪታል ዶ ሬጎ በተፈረመ ይፋዊ የእውቅና ምስክር ወረቀት ላይ፣ መሥሪያ ቤቱ ክላይሜት ስካነር ከግምገማ ማዕቀፍነት ወደ ዘላቂ ተቋማዊ አሠራር እንዴት መሸጋገር እንደሚችል ዓለም አቀፍ ምሳሌ መሆኑ እንደተመሰከረም ተጠቅሷል።
ይህም የዋና ኦዲት ተቋማት በአየር ንብረት አስተዳደርና ተጠያቂነት ረገድ ያላቸውን ሚና የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ስኬት የኢትዮጵያ ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት በአካባቢ ኦዲት ዘርፍ እያደገ የመጣውን ዓለም አቀፋዊ የመሪነት ሚና እንዲሁም በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ዘላቂ ተጠያቂነትን ለማስፈን ያለውን ቀጣይ ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል።
ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...
Oct 20, 2026
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...
Oct 9, 2026
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...
Sep 30, 2026
ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...
Sep 20, 2026