የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 57 ሄክታር የሚሸፍነውን አዲስ የኮሪደር ልማት በይፋ ሥራ አስጀመሩ

Nov 19, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 9/2019 (ኢዜአ) :- በአዲስ አበባ 57 ሄክታር የሚሸፍን አዲስ የኮሪደር ልማት ዛሬ በይፋ ሥራ ማስጀመራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ይፋ በተደረጉት የኮሪደር ልማት ሥራዎች ላይ በመመሥረት ዛሬ የተጀመረው ይህ ልማት፤ ከቦሌ መድኃኔዓለም በጎላጉል እስከ እንግሊዝ ኤምባሲ፣ ከቦሌ መድኃኔዓለም እስከ ሞኤንኮ፣ ከቦሌ ትምህርት ቤት እስከ አደይ አበባ ሞዴል መንደር፣ ከኢምፔሪያል ሆቴል እስከ ሻላ ፓርክ፣ ከቺቺኒያ እስከ ቦሌ ሩዋንዳ፣ ከአደይ አበባ ስታዲየም እስከ ቦሌ መንገድ እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን እንደሚያካትት ገልጸዋል።

ይህ የኮሪደር ልማት ለአረንጓዴ እና ዘመናዊ የከተማ ልማት አዲስ መሥፈርት የሚያስቀምጥ መሆኑን አመለክተዋል።

ፕሮጀክቱ ዘመናዊ መንገዶችን፣ ሰፋፊ የእግረኛ መንገዶችን፣ የብስክሌት መሥመሮችን፣ የመሬት ውስጥ መሠረተ ልማቶችን፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እና ከ5,000 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችሉ የመኪና ማቆሚያዎችን እንደሚያካትት ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፕሮጀክቱ የታደሱ ትምህርት ቤቶችን፣ ቤተ መጻሕፍትን፣ የመጨዋቻ ሥፍራዎችን፣ የስፖርት ሜዳዎችን፣ ካፌዎችን፣ ሬስቶራንቶችን እና ፕላዛዎችን የያዘ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሰዎችን፣ ሰብአዊ ክብርን እና የኑሮ ጥራትን የከተማ ልማት ዋነኛ ማዕከል ማድረጉን አመልክተዋል።

የከተማ ልማት ጥራት የአንድን ሀገር ምርታማነት፣ የሰው ልጅ ክብር፣ ማኅበራዊ ሥርዓት እና የአካባቢን ችግር የመቋቋም ዐቅም መገለጫ እየሆነ መምጣቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በመሆኑም የመደመር መንግሥት የከተሜነት ዕሳቤ፣ ከተሞችን የሥራ ፈጠራ፣ የንግድ፣ የዕውቀት፣ የባህል፣ የተቋማት እና የሥራ ዕድል ምርታማነት ማዕከላት እንዲሆኑ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ይህም ለወደፊት የሕዝብ ቁጥር ዕድገት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ ክስተቶች እና ለመሠረተ ልማት ፍላጎቶች ቀጣይነት ባለው መልኩ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ በዕቅድ የተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ይህ ሥራ ከመሠረተ ልማት ግንባታ በላይ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለአዲስ አበባ እና ለኢትዮጵያ ከተሞች መጻኢ ዕድል የተነደፈ ሰፊ ራዕይ አካል መሆኑን፣ ይኸውም ምርታማነትን፣ አካታችነትን፣ አረንጓዴነትንና የማይበገር ልማትን ያካተተ እንደሆነ ገልጸዋል።

ክንውኑም በሕዝቦች ፍላጎት እና በመጪው ትውልድ መሻት ዙሪያ የተቃኘ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026