
ቦንጋ ፤ ጥር 12/2017 (ኢዜአ) ፡- በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ባለፉት ሶስት ዓመታት በክልሉ በተከናወኑ ተግባራትና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው እንዳመለከቱት፤ ብልፅግና ፓርቲ በአንደኛ መደበኛ ጉባኤው ካስቀመጣቸው አቅጣጫዎች መካከል ሕብረብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር፣ ዘላቂና አስተማማኝ ኢኮኖሚ መገንባት ከዋና ዋናዎቹ ይገኙበታል።
አቅጣጫውን ተከትሎ በክልሉ በተከናወኑ ተግባራትም ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል፡፡
የህዝቡን የመልካም አስተዳደር፣ የልማትና የሰላም ጥያቄዎች መሠረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራትም የሕዝቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው ብለዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እራሱን ችሎ እንዲደራጅ መደረጉ መንግስት ለህዝቡ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ያለውን ፍላጎትና በሳል ውሳኔ ሰጪነት ያሳየበት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ባለፉት ሶስት ዓመታትም በክልሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በተደረገው ሰፊ ጥረት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል።
በኢኮኖሚ ረገድም የክልሉ ትልቅ አቅም ለሆነው የግብርናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት በተከናወነው የማዘመን ስራ ምርትናምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል።
በቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ዘርፍም ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል።
በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በማር፣በወተት፣በዶሮና በሌሎች ዘርፎች ተሰፋ ሰጪ ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ በሁሉም አካባቢዎች የማስፋት ስራ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
በማህበራዊ ዘርፍም በትምህርት ፣ በጤናና በበጎ አድራጎት ስራዎች ህብረተሰቡን በማስተባበር በተከናወነ ተግባር የመጣው ውጤት ለቀጣይ አቅም እንደሆነም ገልጸዋል።
የገቢ አቅምን ማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት ሲከናወን የቆየ ተግባር መሆኑን ያነሱት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በ2014 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የነበረውን የገቢ አቅም በተያዘው ዓመት 10 ነጥብ 7 ቢሊዮን ለማሳደግ ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በቀጣም በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን በማጠናከር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል።
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...
Apr 30, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...
Apr 30, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...
Apr 29, 2026
ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርብ እየተደረ...
Apr 20, 2026