የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በከተማው በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተስተዋለውን ክፍተት ለማረም በተሰራው ሥራ ለውጥ መጥቷል

Apr 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም በተሰራው ሥራ ለውጥ መምጣቱን ተሳፋሪዎችና አሽከርካሪዎች ገለጹ።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ በበኩሉ አገልግሎቱን ለማስተጓጎልና ህዝቡን ለማማረር በሚሰሩ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገው ክትትልና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ከወላይታ ሶዶ ከተማ ወደ ሻሸመኔ እና ሀዋሳ ከተሞች ሲጓዙ የነበሩት ወይዘሮ ብዙአየሁ ሊዮን እና ፓስተር ዳዊት ደግሰው የነዳጅ እጥረቱን ምክንያት በማድረግ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሲገጥም የነበረው እንግልት መፈታቱን ተናግረዋል።

የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማስተጓጎል በሞከሩ አሽከርካሪዎች ላይ መንግስት ክትትል አድርጎ የእርምት እርምጃ መውሰድ በመጀመሩ እንግልቱ ከመቅረቱ ባለፈ በተቀመጠው የታሪፍ ክፍያ መጓዝ እንደቻሉ ገልጸዋል።

አስተያየታቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎችም በኩፖን በሚቀዱት ነዳጅ በተቀመጠው ታሪፍ መሰረት የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በከተማው ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መምሪያ ነዳጅ በተራና በኩፖን የሚቀዱበት ሁኔታ መመቻቸቱ ችግሩን እያቃለለው መምጣቱን ገልጸው፣ ህገወጥ ተግባር በሚፈጽሙ አሽከርካሪዎች ላይ በተጀመረው ክትትልና ቁጥጥር ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ መምሪያ ኃላፊ መቅደስ በዛብህ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ወቅታዊውን የነዳጅ እጥረት ምክንያት በማድረግ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስተጓጎል በሞከሩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል።


ከወላይታ ሶዶ መናኸሪያ በ62 የስምሪት መስመሮች የሚነሱ ከ1 ሺህ 500 በላይ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ በኩፖን እንዲቀዱ መደረጉን ገልጸዋል።

በህግ አግባብ የማይንቀሳቀሱትን ለተወሰነ ጊዜ ከስምሪት የማስወጣትና በገንዘብ የሚቀጡበት ስርዓት መዘርጋቱን ገልጸው፣ በኩፖን የቀዱትን ነዳጅ ለታለመለት ዓላማ ያላዋሉ አሽከርካሪዎች መቀጣታቸውን ተናግረዋል።

በዚህም በአሁኑ ወቅት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ሲስተዋል የነበረው ችግር እየተፈታ መምጣቱን ገልጸው፣ ክትትሉ ይጠናከራል ብለዋል።


የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በተለያዩ ማደያዎች ጨለማን ተገን በማድረግ በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ ሲሸጡ የተገኙ ከአምስት በላይ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ተጀምሯል።

እንዲሁም ከህግ ውጭ ሲዘዋወር የነበረ 9ሺህ 700 ሊትር በላይ ናፍጣ እና 2 ሺህ 259 ሊትር በላይ ቤንዚን ተይዞ ለመንግስት ገቢ መደረጉን ገልጸው፣ ነዋሪው ህገወጥ ድርጊትን በመከላከል እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አድንቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026

በዞኑ የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ወደ ስራ ለማሰገባት አስችሏል

አምቦ፤ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሸዋ ዞን የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እን...

Jul 24, 2026

 በዞኑ እየተካሔደ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጎንደር፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ጎንደር ዞን የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የዞኑ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ...

Jul 23, 2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪ ኤክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/2018 ( አዜአ) ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪ ኤክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤሎምቢ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።...

Jul 16, 2026