የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

Jul 27, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ መሆናቸውን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሸገር ከተማ የግብርና ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ ግርማ ኃይሉ ገለጹ።

የሸገር ከተማ የ2018 በጀት ዓመት የ4ኛው ሩብ ዓመት የክትትልና አስፈጻሚ አካላት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።


አቶ ግርማ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ አርሶ አደሩ የሚያካሒደውን የእርሻ ስራ በሜካናይዜሽን በማገዝ እና የግብርና ግብዓቶችን በወቅቱ በማቅረብ ስኬታማ ስራዎችን ማከናወን ተችሏል።

በ2017/18 የምርት ዘመን በከተማዋ 81 ሺህ 538 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማግኘት መቻሉን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በመስኖ ስንዴ ልማት ከ42 ሺህ 613 ሄክታር መሬት በማረስ 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መገኘቱንም አክለዋል።

በተያዘው የመኸር የምርት ዘመንም 95 ሺህ 500 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በተለይም የግብርና ሜካናይዜሽንን በማሳደግ ምርታማነትን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት መቻሉንም ነው የገለጹት።

ከዚህ በተጨማሪ የከተማው አርሶ አደር የክረምቱን ዝናብ ብቻ ከመጠበቅ ወጥቶ በሁሉም ወቅቶች ማምረት እንዲችል የተለያዩ ጥረቶች መደረጋቸውንም ገልፀዋል።

ለዚህም 171 ሚሊዮን ሜትር ኩብ የመስኖ ውኃ በማቅረብ 42 ሺህ 613 ሄክታር መሬት ማልማት መቻሉን ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026