🔇Unmute
አምቦ፤ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሸዋ ዞን የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እንዳስቻለ የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
በምዕራብ ሸዋ ዞን ድሬ ኢንጭን ወረዳ የተገነቡ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች የክልል ፤ ዞን እና የወረዳ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበበ ጨመዳ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፤ በለውጡ ዓመታት የተገነቡ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሕብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስቻሉ ናቸው።
በዞኑ የተከናወኑት የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በህዝብ እና በመንግስት ተሳትፎ እውን ለመሆን መቻላቸውን ነው የተናገሩት።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም ከ 5 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡት የመሰረተ ልማቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ገልጸዋል።
የድሬ ኢንጭን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አራርሳ ሂርጳ በበኩላቸው፤በኦሮሚያ ልማት ማህበር በወረዳው የመማሪያ ክፍሎችና ዘመናዊ ቤተመጽሐፍቶች መገንባታቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም የኮሪደር ልማት ፣የመንገድና የድልድይ ግንባታዎች እንደተካሔዱም ነው የተናገሩት።

በወረዳው በመንግሥት በጀትና በሕብረተሰቡ ተሳትፎ ከ278 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 23 የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገለቱ ቱካ በበኩላቸው፤ በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት በትኩረት የተሰጠ ሲሆን የትምህርት ግብአትን ለማሟላት ቅድሚያ ተሰጥቷል ነው ያሉት።
ለአብነትም በዛሬው እለት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ከተደረጉት የመሰረተ ልማቶች መካከል ለድሬ ኢንጭን ኦልማ አዳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስፈላጊውን ድጋፍ መድረጉን ተናግረዋል ።
ምርቃቱን አስመልክቶ የድሬ ኢንጭን ወረዳ ነዋሪዎች አንዳሉት፤ በአካባቢያቸው የፀጥታ ችግር በመፈታቱ በልማት ሥራዎች ላይ በንቃት ለመሳተፍ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ነው የሚገልጹት።
ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ኡርጌሳ ቶለሳ እና ወይዘሮ ፈይነ ትሪፈሳ ፤ በአካባቢያቸው ለአገልግሎት የበቁ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የማሕበረሰቡን የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄዎች የመለሱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል ።
በተለይ በአካባቢው ሰላምን ለማስፈን በመቻሉ የልማት ስራዎችን ያለምንም ስጋት ለማከናወን እንዳስቻለ አመልክተዋል።

በአሁኑ ወቅትም ለረጅም ጊዜ ሲነሱ የነበሩ የመንገድ፣ የትምህርት እና ሌሎች የልማት ስራዎች ምላሽ በማግኘታቸው ተጠቃሚ ሆነናል ብለዋል።
አምቦ፤ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሸዋ ዞን የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እን...
Jul 24, 2026
ጎንደር፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ጎንደር ዞን የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የዞኑ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ...
Jul 23, 2026
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/2018 ( አዜአ) ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪ ኤክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤሎምቢ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።...
Jul 16, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የቀጣናውን የኃይል ትስስር ይበልጥ በማጠናከር የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ እየሰራች መሆኑን ...
Jul 8, 2026