
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 4/2017(ኢዜአ)፦ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሥርዓትንና ሕግን አክብሮ መተግበር ከተቻለ የዜጎችን፣ የሀገርንና የተቋማትን ተወዳዳሪነት ማሳደግ ይቻላል ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በቀረፀው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ከውጭ ሀገር የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ሥርዓትንና ሕግን አክብሮ መተግበር ከተቻለ የዜጎችን፣ የሀገርንና የተቋማትን ተወዳዳሪነት ማሳደግ ይቻላል ብለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ሥነ-ምህዳሩን ምቹ በማድረግ ኤጀንሲዎች ሚናቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በተጨማሪም ኢንዱስትሪውን ለመቀየር ብቁ የኤጀንሲዎች ስብስብ በማፍራት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በላቀ ትጋት እየሠራ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡
ይሁን እንጂ በዘርፉ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ሚናቸውን በኃላፊነት ከመወጣት ይልቅ ሕጋዊ አሰራርን በማይከተሉ ኤጀንሲዎች ሳቢያ ዜጎችን ለእንግልትና ለስቃይ የሚዳርጉ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ መከሰታቸውን ጠቁመዋል፡፡
መሰል ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን በመከላከል የዜጎችን ክብርና ደህንነት ማዕከል ያደረገ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ሥርዓት እውን ለማድረግ የአዋጅ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም ጠቁመዋል፡፡

ሕጋዊ አሠራርን ተከትለው ለዜጎች ተገቢውን አገልግሎት ለሚሰጡ ኤጀንሲዎች እውቅና መስጠት የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋት ጥናት እየተካሄደ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡
አሁን በሥራ ላይ የሚገኙ ኤጀንሲዎችን በማሰባሰብ የተሻለ አቅም እንዲፈጥሩ የሚያግዝ ወጥ የሆነ አደረጃጀት በቀጣይ ለመፍጠር መታቀዱን መናገራቸውም በመረጃው ተመላክቷል፡፡
የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት በፍጹም ሥነ ምግባር፣ በሃላፊነትና ሀገርን በመውደድ ስሜት ሊተገበር እንደሚገባም ነው ሚኒስትሯ ያሳሰቡት፡፡
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026