የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የቱሪዝም ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ ፈጠራ የተሞላበት የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም ይገባል -የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ

Jul 10, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 1/2017(ኢዜአ)፦ የቱሪዝም ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ ፈጠራ የተሞላበት የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠቀም እንደሚገባ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለፁ።

ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሀገራችን የሚገኙ መዳረሻዎችን እና የቱሪዝም አገልግሎቶችን በተሻለ ሁኔታ በማስተዋወቅ “ቪዚት ኢትዮጵያ" የተሰኘ ሀገር በቀል የግብይት ድረገፅ በይፋ ስራ ጀምሯል።

ቪዚት ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕምቅ ሀብት፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለአለም የሚያስተዋውቅ ድረገፅ መሆኑ ተገልጿል።


በይፋ ማድረጊያ መርሃግብሩ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሀሚድ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የቪዚት ኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና አገልግሎት ሰጪዎችን የሚያስተዋውቅ እንዲሁም ቻት ቦትን ያካተተ ነው ተብሏል።


በዚህ ወቅት የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እንዳሉት ኢትዮጵያ በርካታ የቱሪዝም ፀጋዎች አሏት።

የቱሪዝም ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ ፈጠራ የተሞላበት የቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ቪዚት ኢትዮጵያ የቱሪዝም መዳረሻዎችን የተመለከተ ወቅታዊና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ማቅረብ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።

የቱሪዝም ዘርፍ ተዋንያንን በአንድ በይነ መረብ የሚያስተሳስር ነው ብለዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሀሚድ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የበለፀገ የባህል ስብጥርና የቱሪዝም ሀብት ያላት አገር መሆኗንም ገልጸዋል።


ያለንበት የዲጂታል ዘመን ጎብኚዎች ባሉበት በመሆን ቪዚት ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፉን አለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉበት ነው ብለዋል።

ቪዚት ኢትዮጵያ ደህንነቱ የተጠበቀና ተጠቃሚን ማዕከል ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026