የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የአፍሪካ አገራት የጣና ፎረም ምክረ ሀሳቦችን በመተግበር ለአህጉሪቷ ለውጥ በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል

Oct 27, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 16/2018 (ኢዜአ)፡-የአፍሪካ አገራት የጣና ፎረም ምክረ ሀሳቦች በመተግበር ለአህጉሪቷ ለውጥ በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ ገለጹ።

በባህር ዳርና አዲስ አበባ ከተሞች ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 11ኛው ከፍተኛ ደረጃ ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል።

"አፍሪካ በተለዋዋጩ ዓለም ሥርዓት" በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ፎረም፤ በአፍሪካ ሠላምና ደህንነት ጋር በተያያዘ ያሉ ችግሮች፣ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ በትኩረት መክሯል።


አፍሪካ በኢኮኖሚ እንዴት ራሷን መቻል አለባት? ምን ዓይነት እርምጃዎች ያስፈልጋሉ? የሚሉ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ በአፍሪካ ያሉ ወጣቶችና ሴቶችን ጨምሮ አካታች ሥርዓት መዘርጋት ለነገ የሚባሉ ጉዳዮች እንዳልሆኑ በፎረሙ በሰፊው ምክክር ተካሂዶበታል።

የማላዊ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የጣና ፎረም የቦርድ አባል ጆይሴ ባንዳ በፎረሙ መዝጊያ ላይ እንዳሉት፤ 11ኛው የጣና ከፍተኛ ደረጃ ፎረም ስኬታማ ሆኖ ተጠናቋል።

የፎረሙ መሪ ሀሳብ አፍሪካ በተለዋዋጩ ዓለም ሥርዓት እንደ አህጉር ልንነጋገርበት የሚገባ ወቅቱን የጠበቀ ጽንሰ ሀሳብ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ወደ ዲጂታል የሚደረገው ሽግግር፣ የተፈጥሮ ሀብትን በፍትሃዊነት እና ዘላቂነት ተደራሽ ማድረግ ትኩረት የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዓለም በፍጥነት እየተለወጠች መሆኑን አስታውሰው፤አፍሪካም እየተለወጠ ላለው የዓለም ሥርዓት የሚመጥን እንቅስቃሴ ማድረግ አለባት፤ ለዚህ ደግሞ በጣና ፎረም የሚቀርቡ ምክረ ሀሳቦችን ወደ ተግባር በመቀየር ረገድ ከአፍሪካ አገራት በቁርጠኝነት መሥራት ይጠበቃል ብለዋል።

አፍሪካ ለማሳካት ያስቀመጠቻቸው ውጥኖች ያለ ወጣቶች ተሳትፎ እውን ሊሆን እንደማይችል አመልክተው፤በአፍሪካ በሁሉም መስክ የሚከናወኑ ተግባራት ወጣቶችን ማዕከል ያደረጉ ሊሆኑ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በፎረሙ ላይ የተለያዩ አገራት መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ልዩ መልዕክተኞች ምሁራንን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በከተማው በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተስተዋለውን ክፍተት ለማረም በተሰራው ሥራ ለውጥ መጥቷል

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...

Apr 30, 2026

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀጣናዊ ዘላቂ ሰላምና እድገትን በምርምር ማገዝ አለባቸው

ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...

Apr 30, 2026

የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...

Apr 29, 2026

‎ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ ርብርብ እየተደረገ ነው 

‎ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርብ እየተደረ...

Apr 20, 2026