የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ነዋሪዎች የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ ምቹ መደላድል ፈጥሯል -የአዳማ ከተማ ከንቲባ

Oct 29, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፤ ጥቅምት 19/2018(ኢዜአ)፡- የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ነዋሪዎች የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ ምቹ መደላድል የፈጠረ መሆኑን የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ አስታወቁ።

በከተማዋ የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል ።

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ በወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ የተሟላ መሰረት ልማት ያላት ውብ፣ ንፁሕና ያማረች አዳማን ለመገንባት የተጀመረው ስራ በሕዝቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ነዋሪዎች የልማት ተጠቃሚነት በተሻለ ደረጃ ይበልጥ ለማሳደግ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስታውቀዋል።

ይህም ልማት 19 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት እና 23 ሜትር ስፋት ያለው የአስፋልት ኮንክሪት፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ ግንባታ መሆኑን ገልጸዋል።

መንገዱ ከዛሬ ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች፣ ለብስክሌትና ለእግረኞች ክፍት መሆኑንም ከንቲባ ሃይሉ ጀልዴ ይፋ አድርገዋል።

ክፍት ከተደረጉት መሰመሮች ውስጥ ከኦሮሚያ ፖሊሲ ኮሌጅ እስከ ደራርቱ አደባባይ ያለው ይገኝበታል።

የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማቱ ሥራ በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የተቀመጠውን ደረጃ አሟልቶ በጥራት መከናወኑን ጠቅሰው፤ በተጨማሪም ስማርት የመብራት ምሰሶዎች፣ አረንጓዴ ፓርኮችና ተያያዥ የመንገድ ዳር የማስዋብ ተግባራት መከናወናቸው አንስተዋል።

በመሰረተ ልማት፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት የተለወጠችና ያደገች ከተማን ለትውልድ ለማስተላለፍ ግብ አድርገን እየሰራን ነው ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ከንቲባው፤ ባለሃብቶችና ነዋሪዎችን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በልማቱ ላይ ሲያደርጉ የቆዩትን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ አማን ሲራጅ በሰጡት አስተያየት፤ ከተማዋ አሁን የሚመጥናትን ልማት እያገኘች ጥሩ ገፅታ እየተላበሰች ትገኛለች ብለዋል።

በከተማዋ ከዋናው መስመር ጀምሮ የበስክሌትና እግረኛ መንገድ እንዳልነበረ አስታውሰው፤ አሁን የኮሪደር ልማት በመሰራቱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል።

አቶ ወሰኔ ቶሎሳ በበኩላቸው፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በከተማዋ የተከናወኑና በመከናወን ላይ የሚገኙ የልማት ተግባራት አበረታች መሆናቸወን ተናግረዋል።

ከመንግሥት ጎን በመሆን የተጀመሩ የልማት ተግባራት ይበልጥ በተሻለ ደረጃ እንዲያድጉ ድጋፋቸውን በትብብርና በቅንጅት እንደሚያጠናክሩም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል።

የመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት በተደረገበት ሥነ-ሥርዓት ላይ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026