🔇Unmute
ሆሳዕና /ቦንጋ ፤ጥቅምት 20/2018 (ኢዜአ)፡ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞን ለማፋጠን መሰረት በሚጥሉት ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የሆሳዕናና የቦንጋ ከተሞች ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርላማ ከህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የሚተገበሩት ግዙፍ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማህበራዊ መጻኢ ዕድል መወሰን የሚችሉ ናቸው ማለታቸው ይታወሳል።
ፕሮጀክቶቹ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ወጣቶች የስራ ዕድልን ከመፍጠር ባሻገር ምርትና ምርታማነትን በእጥፍ ሊያሳድጉ እንደሚችሉ መግለጻቸውም እንዲሁ።
በጉዳዩ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የሆሳዕናና የቦንጋ ከተሞች ነዋሪዎች እንዳሉት ፕሮጀክቶቹ ያላቸው ተስፋ የሚያጓጉ እና ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት የዕድገት ደረጃ ወደ ከፍታ የሚወስዷት በመሆናቸው ለተግባራዊነታቸው የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ተዘጋጅተዋል፡፡
አስተያየታቸውን ከሰጡ በሆሳዕና ከተማ የቦብቾ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ቸርነት ሰዎሬ እንደገለፁት፤ መተባበር ለኢትዮጵያ ከድህነት የመውጫ አንዱ መንገድ መሆኑን ከታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ተሞክሮ የተወሰደበት ነው፡፡
ይህም ኢትዮጵያ ሀብቷን በጋራ በማልማት የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች እውን በማድረግ የማንሰራራት ጉዞዋን ማፋጠን አንደሚቻል መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሌላኛዋ የጀሎ ናረሞ ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ አረጋሽ ካሳ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ከተባበርን ታሪክ መስራት እንደምንችል የሚያስረዱ ብዙ የታሪክና የልማት ተግባራት መኖራቸውን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለምክር ቤቱ ከሰጡት ማብራሪያም የሀገሪቱን የልማት ጉዞ የሚያሳልጡ የቱሪዝም፣ የኢንዱስትሪና የግብርና ልማቶች እንዲጠናከሩ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ በመጠቆም ፕሮጀክቶቹ የታለመላቸውን ግብ እንዲያሳኩ የሚጠበቅባቸውን ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የቦንጋ ከተማ ነዋሪው አቶ ክፍሌ አለሙ፤ የህዝብን የጋራ ጥቅሞች ለማሳካት በመንግስት የተያዙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ከዳር እንዲደርሱ ሁላችንም በአንድነት የድርሻችንን መወጣት ይገባናል ብለዋል።
የሀገርን ልማት እውን ለማድረግ ሁሉም በተባበረ ክንድ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባው በማመን ለተግባራዊነቱም የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ያስረዱት ደግሞ የቦንጋ ከተማ ነዋሪው አቶ እያዩ ገብረማርያም ናቸው፡፡
በመንግስት የታቀዱ ሜጋ ፕሮጀክቶች እውን መሆንም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ በማፋጠን ለዜጎች ኑሮ መሻሻል ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል፡፡
የፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅም ኢትዮጵያን ከድህነት በማላቀቅ ለትውልድ የሚሻገር ሃብት ለማፍራት የሚያስችል በመሆኑ በተፋጠነ መልኩ እውን እንዲሆኑም የሚጠበቅባቸውን ለመፈፀም ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...
Apr 30, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...
Apr 30, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...
Apr 29, 2026
ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርብ እየተደረ...
Apr 20, 2026