🔇Unmute
አምቦ ፤ጥቅምት22/2018 (ኢዜአ)፡- በምእራብ ሸዋ ዞን በመኸር አዝመራ በ48 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የለማው የቢራ ገብስ እንክብካቤ እየተደረገለት ነው፡፡
በጽህፈት ቤቱ የአዝዕርት ልማት ባለሙያ አቶ ደጀኔ ደቡሼ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ የቢራ ገብስን በኩታ ገጠም በማልማት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው፡፡
በዚህም በዞኑ በስፋት ከሚመረተው የጤፍና ስንዴ ልማት በተጓዳኝ አርሶ አደሩ የቢራ ገብስ እንዲያመርት የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።
በመኸር አዝመራም በዘር ከተሸፈነው 48 ሺህ ሄክታር መሬት ከ1 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገኝም አስረድተዋል።
ምርታማነቱን ለማሳደግም የተሻሻሉ የቢራ ገብስ ዝርያዎችን ማቅረብ፣ የግብዓት አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግና በኩታ ገጠም የማደራጀት ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡
የቢራ ገብስ ልማቱ ወልመራ፣ አዳ በርጋ ፣ ጅባት፣ ጀልዱ፣ ድሬ እንጪኒ፣ ኤጄሬና ኤጀርሳ ለፎ ወረዳዎች በስፋት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።
ዘንድሮ የአየሩ ጸባይ ለእርሻው ተስማሚ በመሆኑ ምርቱ በጥሩ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው በልማቱ ከ29 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አርሶ አደሩ ዘመናዊ የግብርና አሰራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ እየሰራ በመሆኑ በአሁኑ ወቅት የቢራ ገብስ ምርታማነትን በሄክታር 37 ኩንታል ማድረስ መቻሉንም አስረድተዋል።
በአርሶ አደሮቹ ጥራቱን ጠብቆ የሚመረተው የቢራ ገብስ ለብቅል ፋብሪካዎች ግብዓት የሚውል ሲሆን ባለፈው ዓመትም የተሻለ ምርት መገኘቱን አስታውሰዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026