የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ቴሌብር የፋይናንስ ተደራሽነት እና አካታችነትን ለማስፋት አስችሏል 

Nov 21, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 11/2018(ኢዜአ)፦ቴሌብር ተጠቃሚዎች በቀላሉ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ ተደራሽነትና አካታችነትን ለማስፋት ማስቻሉን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ።

ኢትዮ ቴሌኮም ከአዋሽ ባንክ ጋር በመተባበር "ጥላ" የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት በቴሌብር አማካኝነት አስጀምሯል።

ይህ ትብብር የሀገሪቱን የፋይናንስ አካታችነት ለማስፋት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ኢትዮ ቴሌኮም የሀገሪቷን ዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይ እውን ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

ቴሌብርን በመጠቀም በቀላሉ የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት መቻሉን አመልክተው፤ ይህም ለተጠቃሚዎቹ ምቹ፣ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ተደራሽነት እንዲሰፋ ማድረጉን አንስተዋል።


‎ቴሌብር የቴክኖሎጂ አቅምን ከባንክ ተቋማት የፋይናንስ ልምድ ጋር የተጣመረበት መሆኑን ጠቅሰው፤ የፋይናንስ አገልግሎትን ወደ ህብረተሰቡ በስፋት እንዲደርስ እያደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

‎ከአዋሽ ባንክ ጋር የተደረገው አጋርነትም ሁለቱ ተቋማት የየራሳቸውን ጥንካሬ ለሀገራዊ ልማት ለማዋጣት እንደሚያስችላቸው ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አስረድተዋል።

‎"ጥላ" ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ምቹ፣ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ አገልግሎት የበለጠ ለማስፋት እንደሚረዳ ተናግረዋል።

‎የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፀሀይ ሽፈራው በበኩላቸው፤ "ጥላ" የባንኩን የዲጂታል ለውጥ ለማፋጠን የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።


‎በተለይም በቴሌብር በኩል የሚቀርቡት እንደ ማይክሮ ብድር (Micro Credit)፣ የሞባይል ቁጠባ (Mobile Saving) አገልግሎቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና አነስተኛ ንግድ ለሚሰሩ ትልቅ ዕድል ይፈጥራሉ ብለዋል።

በቀጣይም ሁለቱ ተቋማት ተጨማሪ አዳዲስ እና ፈጠራ ያላቸው የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማጠናከር እንደሚሰሩ ጠቁመዋል።

"ጥላ" የፋይናንስ ዲጂታል አገልግሎት የቁጠባ፣ የግለሰብ ብድር፣ ለአነሰተኛ መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ብድር እና የዲቫይስ ፋይናንስ አገልግሎቶች በአንድ ጥላ ስር ለመስጠት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ ለህብረተሰቡ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

ሰመራ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ለህብረተሰቡ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

May 21, 2026

በከተማው በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተስተዋለውን ክፍተት ለማረም በተሰራው ሥራ ለውጥ መጥቷል

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...

Apr 30, 2026

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀጣናዊ ዘላቂ ሰላምና እድገትን በምርምር ማገዝ አለባቸው

ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...

Apr 30, 2026

የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...

Apr 29, 2026