🔇Unmute
ጊምቢ፤ ሕዳር 19/2018 (ኢዜአ)፦ በተለያዩ ምክንያቶች የተጎዳ መሬትን በተፈጥሮ ማዳበሪያ በማከም ምርታማነቱ እንዲጨምር በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ማሳደጋቸውን የምዕራብ ወለጋ ዞን አርሶ አደሮች ገለጹ።
የጊምቢ ወረዳ አርሶ አደር ወንድሙ በቀለ፤ የግብርና ባለሙያዎችን ምክረ ሃሳብ በመተግበር ለበጋ መስኖ ልማትና ለመጪው መኸር እርሻ የሚውል የተፈጥሮ ማዳበሪያ ከቅጠላ ቅጠሎችና ተረፈ ምርቶች እያዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በተለያየ ምክንያት የተጎዳ መሬትን በተፈጥሮ ማዳበሪያ በማከም ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደቻሉ አስታውሰዋል፡፡

የተፈጥሮ ማዳበሪያን ከአፈር ማዳበሪያ ጋር በማደባለቅ ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደቻሉና ለማዳበሪያ ግዥ ያወጡት የነበረን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ እንደቀነሰላቸው የተናገሩት ደግሞ የላሎ አሳቢ ወረዳ አርሶአደር ወይዘሮ አኩሜ ጫሊ ናቸው፡፡
በየዓመቱ የተፈጥሮ ማዳበሪያ በመጠቀም ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል ።
በምዕራብ ወለጋ ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቡድን መሪ አቶ ወንድሙ ኢተፋ በበኩላቸው፤ በዞኑ በተለያየ ምክንያት ለምነቱን አጥቶ አሲዳማ የሆነ የእርሻ መሬትን በተፈጥሮ ማዳበሪያ የማከም ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

አርሶ አደሩ አሲዳማ መሬቱን በተፈጥሮ ማዳበሪያ ሀርሚ ኮምፖስትና ነጭ ኖራ እንዲያክም የሚያስችሉ የግንዛቤና የክትትል ስራዎች መጠናከራቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህም የአርሶ አደሩን የአፈር ማዳበሪያ ወጪ ለመቀነስ ከማገዙም በላይ የአፈሩ ለምነት እንዲመለስ ማድረጉን ተናግረዋል።
በዞኑ በተያዘው በጀት ዓመት ወደ 21 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የሚጠጋ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት ታቅዶ ወደ 18 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ የሚጠጋውን ማዘጋጀት መቻሉን አስረድተዋል።
ይህም መጠን 596 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት እንደሚያስችል ተናግረው በተፈጥሮው ማዳበሪያ ዝግጅቱም ከ383 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውን አብራርተዋል፡፡
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026