የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ባሕር ዳር ከተማን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

Dec 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

ባሕር ዳር ፤ ታህሳስ 2/2018(ኢዜአ)፡- ባሕር ዳር ከተማን ተመራጭ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም መዳረሻ ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ የልማት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ አስተዳደሩ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ብርሃን ንጉሴ ገለጹ።

‎የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርና የሰሜን ጎጃም ዞን ሰልጣኝ መካከለኛ አመራሮች በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።


‎አመራሮቹ የኢንዱስትሪ መንደርን፣ የኮሪደር ልማት፣ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲዮም፣ መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት መስጫና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙም ታውቋል።

የ‎መምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ ብርሃን ንጉሴ በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት፤ ባሕር ዳርን ለነዋሪዎቿ ምቹና ፅዱ ከተማ ለማድረግ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

‎በተለይ በከተማ አስተዳደሩ 268 የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች በስራ ላይ እንዳሉ ጠቅሰው፤ 108 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ በግንባታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

‎እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርቶችን ከማምረት ባለፈ ለበርካታ ወገኖች የስራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ ሚናቸውን እየተወጡ ይገኛል ነው ያሉት።

‎እንዲሁም በመጀመሪያው ምዕራፍ የተገነባው የኮሪደር ልማት ከጣና ኃይቅ ጋር የሚያስተሳስሩ መንገዶች በመከፈታቸው የከተማዋ ውበት ይበልጥ የተገለጠበት መሆኑን ተናግረዋል።

‎እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ከተማዋ ተመራጭ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም መዳረሻ እንድትሆን እያስቻሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

‎በቀጣይም የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በመደመር መንግስት እይታ በመቃኘት የከተማዋን ዕድገትና ልማት በማፋጠን የሕብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026