🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ታኅሣስ 2/2018(ኢዜአ)፡- ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረበ ያለው የቡና ምርት መጠንና ጥራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የክልሉ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ባለሥልጣን ገለጸ።
ባለፉት አራት ዓመታት በየዓመቱ በአማካይ 52ሺህ 257 ቶን የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አሥራት መኩሪያ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በ2018 በጀት ዓመትም 71ሺህ 400 ቶን የታጠበና ያልታጠበ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱን ጠቅሰው፤ እስካሁን 10ሺህ 21 ቶን ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን አረጋግጠዋል።

በአሁኑ ወቅትም የቀይ እሸት ቡና ምርት አሰባሰብና የታጠበ ቡና ምርት ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።
የዘንድሮውን ዕቅድ ለማሳካት የቡና ግብይትና ዝውውር ሕጋዊ እንዲሆን ብሎም ጥራቱን ለማስጠበቅ በየደረጃው ያለው የቡና ምርት ጥራትና ግብይት ቁጥጥር ግብረ-ኃይል ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
የታጠበ ቡና ምርት አዘገጃጀትና ጥራት አጠባበቅን አስመልክቶ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት በተግባር የተደገፈ ስልጠና መሰጠቱንም አንስተዋል።
በሌላ በኩል በበጀት ዓመቱ እስካሁን በቡና ችግኝ ዝግጅት፣ በቡና ምርት አሰባሰብና ምርት ዝግጅት ለ22 ሺህ 441 ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026