🔇Unmute
ጂንካ፤ ታህሳስ 2/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በበጋ መስኖ የምርት ማሳደጊያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።
በዚህም በክልሉ በበጋ መስኖ 4 ሺህ 482 ሄክታር መሬት በስንዴ እንደሚለማም ተመላክቷል።
ስንዴ አብቃይ ባልሆኑ አካባቢዎች ጭምር የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት በስፋት ተተግብሮ ውጤት እየተገኘበት ይገኛል።
የበጋ ስንዴ ልማቱ ውጤታማ ከሆነባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች መካከል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንዱ ሲሆን በልማቱም ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየታዩ ነው።
ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ግዳልቅ አልቅሚ እንዳሉት በክልሉ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት የተጀመረውን ሀገራዊ ኢንሼቲቭ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችል ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
በተያዘው የበጋ መስኖ የግብርና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ ለዚህም በአርሶና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች 4 ሺህ 482 ሄክታር መሬት ሙሉ የግብርና ፓኬጅ በመጠቀም ይለማል ብለዋል።
በስንዴ ልማቱ 158 ሺህ 492 ኩንታል ምርት ለማግኘት ግብ መጣሉንም አቶ ግዳልቅ ተናግረዋል።
ከመደበኛ የስንዴ ልማቱ በተጨማሪ በመኸር እርሻ በአርሶ አደሮች ማሳ ጭምር የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት ሥራ መከናወኑን አስታውሰው ይህም የምርጥ ዘር አቅርቦትና ጥራት ችግርን በመፍታት የስንዴ ምርታማነትን ያሳድጋል ብለዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮ የበጋ መስኖ ከስንዴ ልማቱ ባሻገር በተለያዩ ሰብሎች ከ150 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን ከ38 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ከክልሉ ግብርና ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026