🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 2/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በዲጂታል ግብርና ላይ የጀመረችው ተግባር ለአፍሪካ የዲጂታል ግብርና ሽግግር በምሳሌነት የሚወሰድ መሆኑን በአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማ፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አከባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ተናገሩ።
በአፍሪካ ህብረት የግብርና፣ ገጠር ልማ፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና ዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የአፍሪካን የግብርና ስርዓት ለመለወጥና የምግብ ዋስትናን ለማረጋግጥ ዲጂታል ግብርናን መተግበር ወሳኝ ነው።
ይህም ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የምርት ብክነትን ለመቀነስ፣ የፋይናንስና የገበያ ተደራሽነትን ማስፋትን ጨምሮ የመቋቋም አቅምን ለመገንባት ቁልፍ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የግብርና ዘርፉን በዲጂታል ስርዓት ለመቀየር የጀመረችው ጥረት አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል።
ዲጂታል ግብርና ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞችን መሠረት በማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለዲጂታል ሽግግርና ለዘመናዊ ግብርና ዕድገት ያላቸው አስተዋፅኦ የጎላ እንደሆነም ነው የተናገሩት።
የግብርና ትራንስፎርሜሽን ጉዞው በዘመናዊ አሰራሮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ተከትሎ ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት የስንዴ ምርትን በእጅጉ ማሳደግ መቻሏን አንስተዋል።
ውጤቱ የተገኘው በዲጂታል ስርዓት የታገዘ የአፈር ካርታ አሰራርና ሌሎች ዘመናዊ የግብርና ስልቶችን መጠቀም በመጀመሯ እንደሆነ ገልፀዋል።
በተጨማሪም አርሶ አደሮች በዲጂታል ቴክኖሎጂ በመታገዝ ስንዴና ካሳቫ የሚዘሩበትን አካባቢ በግልጽ ለማወቅ እያስቻላቸው ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ይህም የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዲጂታል ግብርና የጀመረችው ተግባር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ ተደርጎ የሚወሰድና ለአህጉሪቱ የግብርና ዘርፍ አዲስ ተስፋ የፈጠረ መሆኑን አስታውቀዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026