🔇Unmute
መቱ ፤ ታኅሣስ 30/2018(ኢዜአ)፦ በመቱ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የመሠረት ልማት ግንባታዎች የነዋሪውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ ኦልጂራ ሒርኪሳ እንዳሉት፤ በከተማዋ እየተገነቡ ያሉት የመንገድ፣ የጤናና የትምህርት ተቋማት የነዋሪውን የልማት ጥያቄ የሚመልሱ ናቸው።

የፕሮጀክቶቹ መገንባት ለዜጎች የስራ ዕድሎች የፈጠሩና የከተማዋን ገጽታ በመቀየር ለቱሪስት መስህብነት ተጨማሪ አቅም እንደሚሆኑ አክለዋል።
የመቱ የከተማ ነዋሪው አቶ ታከለ ጌትነት በበኩላቸው፤ በከተማዋ ቀደም ባሉት አመታት ተሰርተው በእድገቷ ልክ ባለ መታደሳቸውና በአዲስ የተጀመሩትም በወቅቱ ባለመጠናቀቃቸው ለነዋሪው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆነው መቆየታቸውን አንስተዋል።
በአሁኑ ወቅት ግን ከተማ አስተዳደሩ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የጀመራቸው ስራዎች ለህብረተሰቡ የልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ምላሽ መስጠታቸውን ተናግረዋል።
እሳቸውም ከከተማዋ አስተዳደር ጋር በመተባበር ለከተማዋ እድገት የበኩላቸውን እያበረከቱ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የመቱ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከበደ ነገሱ እንደተናገሩት፤ የከተማዋን ነዋሪ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቷል።

ለአብነትም በበጀት ዓመቱ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ቀደም ሲል የተጀመሩና በአዲስ መልክ እየተገነቡ የሚገኙ 44 ፕሮጀክቶችን አጠናቅቆ ወደ ስራ ለማስገባት ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።
በከተማዋ ከሚገነቡት ፕሮጀክቶች መካከል የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ጤና ጣቢያ፣ የተቀናጀ የከተማ ግብርና፣ ቡኡረ-ቦሩ እና መደበኛ ትምህርት ቤቶች፣ የገበያ ማዕከል፣ ሼዶችና የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙበት አክለዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026