🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦ የመንግስት የልማት ድርጅቶች በኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ ይበልጥ በማጠናከር ከኢትዮጵያ ተሻግረው በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
በ2014 የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 41 የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ወደ አንድ በመሰብሰብ የኢትዮጵያን ሃብት የማወቅ፣ ተበታትኖ የቆየውን ሃብት በተደራጀ መንገድ የማስተዳደር ስራ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።
ተቋሙ ከመመስረቱ አስቀድሞ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የፋይናንስ፣ የኦዲት፣ የካፒታል፣ የብድር ጫና እና የኮርፖሬት አስተዳደር ችግር ውስጥ የነበሩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚብሩክ ታዬ (ዶ/ር) አስታውሰዋል።
አሁን ላይ በኢትዮጵያ ኢንቨትመንት ሆልዲንግስ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ዘመናዊ የባለቤትነት፣ የአስተዳደር ስርዓት እና ዓለም አቀፍ የኮርፖሬት አስተዳደር ስርዓት ተዘርግቶላቸዋል ብለዋል። በተጨማሪም ዘመናዊ የኦዲት ስርዓት እንዲከተሉ መደረጉንም አስታውቀዋል።
ይህም ተቋማቱ ከኪሳራ ወጥተው ወደ ትርፋማነት እንዲሸጋገሩ አስችሏል ነው ያሉት። ባለፉት አራት ዓመታትም የተቋማቱ አጠቃላይ ገቢ ቀድሞ ከነበረበት ከ704 ቢሊየን ብር ወደ 6.1 ትሪሊየን ብር ማሳደግ መቻሉን ጠቁመዋል።
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ዛሬ ላይ በ36 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በእነዚህ ተቋማት ስር ያለው የሃብት መጠንም 8.2 ትሪሊየን ብር መድረሱን አስታውቀዋል።
በዚህም የመንግስት የልማት ድርጅቶች በኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸውን አበርክቶ ይበልጥ በማጠናከር ከኢትዮጵያ ተሻግረው በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪ እና ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ እየተሰራ ነው ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...
Apr 30, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...
Apr 30, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...
Apr 29, 2026
ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርብ እየተደረ...
Apr 20, 2026