የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በዘርፉ በተደረጉ ማሻሻያዎች የኔትወርክ ተደራሽነት እና የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል

Jan 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥር 7/2018(ኢዜአ)፦በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ‎ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎች አዳዲስ ኦፕሬተሮችን ወደ ስራ ከማስገባት ጀምሮ የኔትወርክ ተደራሽነት እና የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል ሲሉ‎የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርባልቻ ሬባ (ኢንጅነር) ገለጹ፡፡

ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የሚያስችል ተቋማዊ አሰራርን መከተል ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።

‎ለዚህም በዘርፉ የሚሰማሩ አገልግሎት ሰጪዎች ፈቃድ መስጠት፣ መከታተልና መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን ‎የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተርባልቻ ሬባ (ኢንጅነር) ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ዘርፉ በራሱ እድገት እንዲያስመዘግብ ከማድረግ ባለፈ ለሌሎች ዘርፎች እድገት አስቻይ በመሆኑ በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።

‎አሁን ላይ በዘርፉ የተደረጉ ማሻሻያዎች አዳዲስ ኦፕሬተሮችን ወደ ስራ ከማስገባት ጀምሮ የኔትወርክ ተደራሽነት እና የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስታውቀዋል።

ይህ ዘርፍ በራሱ ከሚያስመዘግበው ውጤት ባለፈ ለሌሎች ዘርፎች አስቻይ በመሆኑ በዘርፉ ላይ የሚሰራው ስራ ወሳኝ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

በተለይ ቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለፋይናንስ ተደራሽነት፣ ቅልጥፍና እና ዘመናዊ አገልግሎት እየሰጠው ያለው አገልግሎት ተጠቃሽ ነው ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026