🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ጥር 25/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና ዩናይትድ ኪንግደም ሰላምና ልማትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች አጋርነታቸውን ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ከዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር ጋር በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተወያይተዋል።
ውይይቱ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ በቆየው የአፍሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም አጋርነት ያተኮረ ነው።
ሁለቱ ወገኖች የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ እና ህግን መሰረት ያደረገ ዓለም አቀፍ ስርዓት ለመጠበቅ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ዩናይትድ ኪንግደም ከአፍሪካ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ትስስር ያደነቁ ሲሆን በዓለም ላይ ያላትን ገንቢ ሚና እና ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ጋር በጤና፣ ትምህርት፣ የአየር ንብረት ምላሽ እና ንግድ ያላትን ትብብር አንስተዋል።
ሀገሪቷ ለአፍሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (አፍሪካ ሲዲሲ) በአደጋ ጊዜ ዝግጁነት እና ምላሽ እንዲሁም በሶማሊያ ለአፍሪካ ህብረት የድጋፍ እና የማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ድጋፍ እያደረገች እንደምትገኝም አመልክተዋል።
የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር የአፍሪካ ህብረት በዓለም ዲፕሎማሲ፣ ቀጣናዊ ሰላም እና ልማት ያለውን ሚና አድንቀዋል።
ሁለቱ ወገኖች የአፍሪካ ህብረት እና ዩናይትድ ኪንግደም በሱዳን፣ በሳሄል ቀጣና እና በሶማሊያ ያለውን የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026