🔇Unmute
ዲላ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦የዓድዋ ድል የትናንት ታሪካችን ብቻ ሳይሆን የነገ እድገትና አንድነታችን መሰረት ነው ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ገለጹ።
ኢትዮጵያውያን በዓድዋ ያሳዩትን አኩሪ ገድል የዘመኑ ትውልድ በልማቱ ሊደግመው ይገባል
130ኛው የዓድዋ ድል በዓል "ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ" በሚል መሪ ሀሳብ በዲላ ከተማ ተከብሯል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ የዓድዋ ድል የሀገር ማንሰራራት የሚጸናበት የነጻነት ቀን ነው።
ዓድዋ ያለፈ የድል ታሪካችን ብቻ ሳይሆን የነገ እድገትና አንድነት መሰረት መሆኑን አንስተው፣ በአሁኑ ወቅትም ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የልማት ጉዞን ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።
ህብረ ብሔራዊነትን ለአብሮነትና ለሀገራዊ እድገት በመጠቀም በተለያዩ የልማት ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በተለይ በክልሉ የሚገኙ ጸጋዎችን አቀናጀቶ በመጠቀም ከራስ ባለፈ ትርፍ አምራች የመሆን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ዓድዋ ጀግኖች አርበኞች የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር ከፍለው የጥቁር ህዝብን ትርክት የቀየሩበት ደማቅ የጀግንነት ታሪክ መሆኑን ያነሱት ደግሞ የዲላ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ታሪኩ በየነ ናቸው።
ድሉ የነጻነትና የአንድነት ምልክት መሆኑን አንስተው እኛም ከዓድዋ ጀግኖች በመማር የድህነት ታሪካችንን መቀየር አለብን ብለዋል።
በዲላ ከተማ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን በማጠናከር እድገትን ለማፋጠን በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።
የዓድዋ ድል በፓናል ውይይትና በተለያዩ ኪናዊ ዝግጅቶች የተከበረ ሲሆን ከክልል ጀምሮ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የመከላከያ ሠራዊት አባላት ታድመዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026