🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ የካቲት 23/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የቡና ወጪ ንግድ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግና የቡና አቅርቦት ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ትኩረት መሰጠቱን የግብርና ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ገለጹ።
የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ከቡና አምራቾች፣ ላኪዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር በቡና ወጪ ንግድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ባለፉት ዓመታት በቡናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን በመገምገም፣ በቀጣይ ወራት ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡
የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ በወቅቱ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ምሰሶ የሆነውን የቡና ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው።
ተለዋዋጭ የሆነውን የዓለም ገበያ ታሳቢ በማድረግ የቡና ምርትን በጥራትና ፍጥነት ለገበያ ማቅረብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቅሰው፤ በቀጣይ ሦስት ወራት በአርሶ አደሮች፣ በአቅራቢዎችና ላኪዎች መጋዘን የሚገኘውን ቡና ጥራቱን ጠብቆ በፍጥነት ለዓለም ገበያ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይ ቡናን ጥራቱን በመጠበቀ ወደ ውጭ ለመላክ ርብርብ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተው፤ በዚህም የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ወደ አዲስ ከፍታ ለማድረስ የተቀናጀ ስራ ማከናወን እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።
በቡና እሴት ሰንሰለት ውስጥ የሚሳተፉ አርሶ አደሮች፣ አቅራቢዎችና ላኪዎች በእኩልነት ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር ይበልጥ እንዲጠናከር ይሰራልም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ መድረክ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማስቀጠል ከአርሶ አደሩ እስከ ውጭ ገበያ ያለው የጥራት ቁጥጥር ስርዓትን ይበልጥ ለማዘመን የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን የቡና ወጪ ንግድን በዓለም ገበያ ተወዳዳሪነቱን ለማሳደግና የቡና አቅርቦት ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ለተቀናጀ ጥረት ትኩረት መሰጠቱንም ተናግረዋል።
በተለይም የዓለም የቡና ዋጋ ሁኔታን በመከታተል ለባለድርሻ አካላት በየጊዜው ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤ በተለይ ቡና ወደ ማዕከላዊ ገበያ በፍጥነት እንዲቀርብ የተለያዩ ስራዎች እንደሚከናወኑ አመልክተዋል።

የኢትየጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ 600 ሺህ ቶን ቡናን ወደ ውጪ በመላክ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ነው፡፡
የተያዘውን ግብ ለማሳካትም የቡና አምራቾችና ላኪዎች በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ መንግስትም ግቡን ለማሳካት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የቡና ላኪዎች በሰጡት አስተያየትም፤ በመንግስት በኩል ዘርፉን ለማሳደግ የሚደረጉ የማሻሻያ ስራዎች የሚበረታቱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026