🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 1/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በሸገር ከተማ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማሳደግ እና ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር በኩል አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የሚታዩ መዋቅራዊ ችግሮችን በመፍታት በኩል ውጤታማ ሥራዎች እንዲመዘገቡ እያስቻለ ይገኛል፡፡
ንቅናቄው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ከመተካት፣ የኤክስፖርት ገቢን ከማሳደግ፣ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ከማሻሻል አንጻር እንዲሁም ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር አኳያ አመርቂ ውጤት እያስገኘ ነው፡፡
የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) ንቅናቄው በከተማው ኢንዱስትሪዎች በስፋት ወደ ሥራ እንዲገቡና ውጤታማ እንዲሆኑ ትልቅ አቅም መፍጠሩን ገልጸዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከምስረታው ጀምሮ ለአምራች ዘርፉ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመው የመሬት አቅርቦት ችግርን ከመፍታት ባለፈ፣ ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት የሚሆኑ የማስፋፊያ ቦታዎች እንዲመቻቹ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
የግንባታ ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ሳይገቡ የቆዩ ባለሀብቶች በፍጥነት ወደ ግንባታና ወደ ምርት ሂደት እንዲሸጋገሩ መደረጉን ጠቅሰው በዚህም ከ800 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
አምራቾች የብድር አቅርቦት እንዲያገኙ ከማድረግ አንጻር በዘንድሮው በጀት ዓመት ግማሽ ዓመት ብቻ 40 ቢሊየን ብር የሚጠጋ የብድር አቅርቦት መመቻቸቱን ከንቲባው አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በከተማዋ ተጨባጭ ውጤቶችን እያስገኘ መሆኑን ጠቅሰው ሰፊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር በወጪ ንግድ በኩልም አበረታች ውጤቶች እየተመዘገበ መሆኑን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡
በተጨማሪም ዘርፉ የከተማዋን የኢኮኖሚ መዋቅር በመደገፍ በኩል ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ከንቲባው አስታውቀዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ይበልጥ ለማሳደግና ለባለሀብቶች ምቹ አካባቢን ለመፍጠር የሚነሱ ማነቆዎችን የመለየትና የመፍታት ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...
Apr 30, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...
Apr 30, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...
Apr 29, 2026
ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርብ እየተደረ...
Apr 20, 2026