🔇Unmute
ባህር ዳር፤ መጋቢት 1/2018( ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የገጠሩን ማህበረሰብ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት በማሳደግ አኗኗሩን ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ እስካሁን በተደረገ ጥረት ከ234 ሺህ 600 የሚበልጡ የኃይል አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን ለተጠቃሚዎች ማሰራጨት መቻሉም ተገልጿል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ጥላሁን ሽመልስ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ የኃይል አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን ተደራሽ ለማድረግ በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።
ቴክኖሎጂዎቹ የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗር በማዘመን ረገድ ያላቸውን የጎላ ሚና ግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ አማራጮች ስርጭት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህም ባለፉት ሰባት ወራት በተሰራ ስራ 100 ሺህ የሚደርሱ ኃይል ቆጣቢ ምድጃዎችን ለማሰራጨት ታቅዶ ከእቅድ በላይ 109 ሺህ ያህሉን ማሰራጨት ተችሏል ብለዋል።
እንዲሁም 54 ሺህ ኃይል ቆጣቢ የኤሌክትሪክ ምጣድና ምድጃዎች፣ ከ70 ሺህ 400 በላይ በፀሐይ ብርሃን ሃይል የሚሰሩ ለመብራትና መሰል አገልግሎት የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
በዚህም ለማገዶ ተብሎ የሚወድመውን የደን ምንጣሮ ለመከላከል ከማገዙም ባለፈ አርሶ አደሩ ባለበት ሆኖ የአማራጭ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻሉን አስረድተዋል።
ይህም ኃይል ለማግኘት በባህላዊ መንገድ ይደርስ የነበረውን የድካም፣ ኢኮኖሚያዊ ጫናና የጤና እክል ለመከላከል እንዳስቻለም አብራርተዋል።
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...
Apr 30, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...
Apr 30, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...
Apr 29, 2026
ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርብ እየተደረ...
Apr 20, 2026