የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የባህር በር ባለቤትነት የኢኮኖሚ ዕድገትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስቀጠል ወሳኝ ነው

Mar 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ ዕድገት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስቀጠል ወሳኝ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የምጣኔ ሀብት ምሁራን ገለጹ።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የብሄራዊ ጥቅምና የህልውና ጉዳይ ነው

የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የባህር በር አልባ መሆኗ ለወጪና ገቢ ንግድ የምታወጣውን ወጪ እጅግ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል።

በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሀመድ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በፈጠራና በፍጥነት ላይ የተመሰረተ አስደማሚ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸዋል።


ይህ ዓይነቱ ግዙፍ ዓመታዊ ዕድገት በዓለምም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ በጥቂት ሀገራት ብቻ የሚታይ መሆኑን የጠቀሱት ተመራማሪው፣ ሀገሪቱ ያላትን ከፍተኛ ምርታማነትና የልማት ስኬት አብራርተዋል።

ይሁን እንጂ ሀገሪቱ አሁን ያላትን እምቅ አቅም እና የህዝብ ቁጥር ያገናዘበ ዕድገት እንዲኖራት ለበርካታ አስርት ዓመታት ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ እንደሚላት አመልክተዋል።

ለዚህም እንደ ቬትናም ያሉ ሀገራትን ተሞክሮ በማንሳት፣ የወደብ ተደራሽነት ለወጪ ንግድ ዕድገትና ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ያለውን ወሳኝ ፋይዳ በአብነት ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ወደብ ቢኖራት አሁን የሚታየውን ኢኮኖሚያዊ እድገት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያሳድገው የጠቆሙት ተመራማሪው፤ በዚህም የወደብ ጉዳይ ለሀገራዊ ጥቅምና ለዜጎች ኑሮ መሻሻል መሰረታዊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የባህር በር ባለቤትነት መረጋገጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ለመጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ዘላቂና አስተማማኝ የሆነ የኢኮኖሚ መፍትሄ እንደሚያመጣ አስረድተዋል።


በኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ባለሙያዎች ማህበር ከፍተኛ ተመራማሪ ሞላ አለማየሁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣የባሕር በር አለመኖር የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ በሌሎች ሀገራት ፍላጎት ላይ ጥገኛ እንዲሆን በማድረግ በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑ አስረድተዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ መብቷ የሆነውን የባሕር በር ባለቤትነት ካረጋገጠች የንግድ እንቅስቃሴዋን በማሳለጥ የትራንስፖርት ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የባሕር በር ባለቤት መሆን የንግድ ተወዳዳሪነትን ከመጨመሩም በላይ የኢኮኖሚውን እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ መሠረታዊ መፍትሔ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026