የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በዞኑ ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሃን በመጠቀም የመስኖ ልማት በስፋት እየተከናወነ ነው

Mar 25, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወልዲያ፤ መጋቢት 16/2018(ኢዜአ)፦ በሰሜን ወሎ ዞን ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሃን በመጠቀም የመስኖ ልማት በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን የተቀረጹ የግብርና ፖሊሲዎችና አዳዲስ ኢንሼቲቮች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው።

በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማትና በዘመናዊ የግብርና አሰራሮች የታየው ለውጥ የሀገሪቱን የምግብ ሉዓላዊነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር ያስቻለ ስለመሆኑ የተገኙ ውጤቶች ያመላክታሉ።

በከፍተኛ ትኩረት የተሰራው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፣ ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን ስንዴ በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ያስቻለ ታሪካዊ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።

የእንስሳትና የዶሮ እርባታ፣ የማር ምርትንና የወተት ልማትን የሚያካትተው የ"ሌማት ትሩፋት" ኢንሼቲቭም የዜጎችን ተጠቃሚነትና የምርት አቅርቦት ለማሻሻል ያስቻለ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት በሁሉም አካባቢዎች በግብርና ልማት የተለያዩ አማራጭ ምርቶችንና ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት በልዩ ትኩረት መከናወኑን ቀጥሏል።

ከዚህ አንፃር በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በተለይም በመስኖ ልማት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ ኢዜአ የግብርና ባለሙያዎችንና አርሶ አደሮችን አነጋግሯል።

በዞኑ ግብርና መምሪያ የመስኖ አግሮኖሚስት ወርቁ ደሳለ፤ በዞኑ የመስኖ ልማትን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ልማት ኢንሸቲቮች መልካም ውጤት እያመጡ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ እና ሌሎችም ምርቶች ላይ የመስኖ አማራጮችን አስፍቶ በመጠቀም ምርታማነትንና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን ጠቅሰዋል።

በዞኑ ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች የከርሰ ምድርና የገጸ ምድር ውሃን በመጠቀም የመስኖ ልማት በስፋት በማከናወን ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም መሰረት በበጋው በ1ኛ ዙር ብቻ 32 ሺህ 525 ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች በመስኖ ማልማት ስለመቻሉ ጠቁመዋል።

አጠቃላይ ምርቱ ሲሰበሰብ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በጉባላፍቶ ወረዳ የአላውሃ ቀበሌ አርሶ አደር ሞላ ገበየሁ እና በወረዳው ውድመን ቀበሌ አርሶ አደር መኮንን አርጋው፤ የምርት ግብዓቶችን በአግባቡ መጠቀም፤ በግብርና ባለሙያዎች ምክርና ድጋፍ ዓመቱን ሙሉ በምርት ሂደት ላይ ትኩረት አድርገን እየሰራን ውጤት እያመጣን ነው ብለዋል።

አርሶ አደሮቹ መሬታቸውን በበጋ መስኖ፣ በዝናብ ወቅት ደግሞ በመደበኛ የግብርና ስራዎች ላይ በማተኮር እንዲሁም በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026