🔇Unmute
ሀላባ ቁሊቶ፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፡- በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር በወተትና በዶሮ ልማት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን ኢዜአ ያነጋገራቸው የመርሐ-ግብሩ ተሳታፊዎች ገለጹ።

ወጣት አብድልቃድር ሲራጅ እንደገለጸው፤ ከጓደኞቹ ጋር ተደራጅተው በተሠማሩበት የዶሮ ዕርባታ ዘርፍ ውጤታማ ሆነዋል።
በዚህም መሠረት አሁን ከ1 ሺህ በላይ ዶሮዎች እንዳላቸው እና በቀን እስከ 900 እንቁላል ለገበያ እያቀረቡ መሆናቸውን አረጋግጧል።

ካፒታላቸው 3 ሚሊየን ብር ማለፉን እና ከ15 ለሚልቁ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠራቸውንም ገልጿል።
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጭ አየለች ካሳ በበኩላቸው፤ በተሠማሩበት የከብት ዕርባታ ዘርፍ ውጤታማ በመሆን አሁን ላይ 10 የወተት ላሞችና 13 ጥጃዎች እንዳሏቸው ገልጸዋል።

በቀን ከ90 ሊትር በላይ ወተት ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያቸውን እያሳደጉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብር በእንስስት ሀብት ዘርፍ ያለውን ዐቅም ወደ ውጤት እንዲቀየር በማስቻል ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የሀላባ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ ሀጂ ኑሪዬ ናቸው።

የዘርፉን ስኬታማነት ለማሳደግ ዝርያ የማሻሻል፣ የእንስሳት ጤና አጠባበቅና አመጋገብ ላይ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ከ17 በላይ የወተት፣ ከ21 በላይ የዶሮ እና ከ10 በላይ የማር መንደሮች መኖራቸውንም አብራርተዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026