የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች

Apr 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

በዮሐንስ ደርበው

✍️ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች

‘በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ’ ከሚለው ብኂል የላቁና ቁጭት የወለዳቸው ኢኒሼቲቮች - የቱሪዝም ፀጋን ከመግለጥ ባለፈ የገቢ መጠንን እንዲሁም የሥራ ዕድልን እያሳደጉ ነው።

ምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ እንደመሆኗ ብዙ ናት። ይህን ሁሉም ሀገራት ስለማያገኙት ዕድለኛም ናት፤ የእኛም ስለሆነች መታደል ነው።

የተለያየ የኑሮ ዘይቤ፣ ባህል እንዲሁም ሁሉንም የዐየር ፀባይ ዐቅፋለች። ደግሞም ልዩ ልዩ የተፈጥሮ አቀማመጥ በልዩነት የተቸራት።

አሥረጂ ማቅረብ ቢያሻ በሀገሪቱ ከፍተኛ ከሆነው ስሜን ተራራዎች እስከ ዝቅተኛው ስፍራ ዳሎል ያለውን የተፈጥሮ ፀጋ መጥቀስ ሁነኛ ምሥክር ነው።

ከሀገራዊ ለውጡ አበርክቶዎች

የዘርፉ ባለሙያዎች ‘ካሎሪ አልባው መድኃኒት’ ይሉታል

የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...!

ከመጋቢት ሥጦታዎች መካከል - የጉባ ብሥራቶች

✍️ የተፈጥሮ ችሮታ ለኢትዮጵያ

ከብዙ ሥጦታዎቿ መካከል ብሔራዊ ፓርኮችን ብቻ ብናነሳ… የኢትዮጵያ የዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን በጀት መድቦ በቀጥታ በሥሩ 11 ብሔራዊ ፓርኮችን እና ሁለት የዱር እንስሣት መጠለያዎች ያሥተዳድራል።

እነሱም፡- 📌 ስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አዋሽ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አብያታ ሻላ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ኦሞ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ገራይሌ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ሃላይደጌ ብሔራዊ ፓርክ፤ 📌 ቃፍታ ሽራሮ ብሔራዊ ፓርክ እንዲሁም 👉 ባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ እና 👉 ሲንቂሌ የቆርኬዎች መጠለያዎች ናቸው።

ብሔራዊ ፓርኮቹና የዱር እንስሣት መጠለያዎቹ የሀገሬው ሀብት ናቸውና፤ እየተንከባከቡ መጠቀም ይገባል።

✍️ መንግሥት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም

ከላይ የተገለጹትን ብሔራዊ ፓርኮችና ሌሎችንም፤ ከቤት እንስሣት ንክኪ ነጻ በማድረግ፣ ከልቅ ግጦሽ እንዲሁም ከሕገ-ወጥ ዐደን ለመጠበቅ መንግሥት ብዙ ገንዘብ ያወጣል። የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ዐቅርቦትንም ያሟላል። ይህም ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ይመሠክራል።

በሌላ በኩል የላሊበላ አብያተክርስቲያናት፣ ሶፍዑመር ዋሻን እና የፋሲል አብያተ መንግሥትን ጨምሮ በየክልሎች የሚገኙ ቅርሶችን በመጠገንም እንዲሁ እየተጋ ነው።

ከአምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎቹ አንዱ የቱሪዝም ዘርፍ ማድረጉም ትኩረቱን ያሳያል። በዚህ ሂደት በየአካባቢው ፀጋዎችን ዕየለየ በርካታ መዳረሻዎችንና የጎብኝ ማረፊዎችን አልምቷል፤ እያለማም ነው። እነዚህም በኢኮኖሚው ብሎም በሥራ ዕድል ፈጠራ ከፍ ያለ ሚና እያበረከቱ ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት፤ በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ የተሠሩ መዳረሻዎችን ለአብነት ብንጠቅስ፤ ‘በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ’ ከሚለው ብኂል የላቁና ቁጭት የወለዳቸው ኢኒሼቲቮች ናቸው። የቱሪዝም ፀጋን ከመግለጥ ባለፈ የገቢ መጠንን እንዲሁም የሥራ ዕድልን እያሳደጉ ነው።

ኢትዮጵያ ዛሬ ነገንም እየሠራች ነውና፤ በቱሪዝሙ ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት በተለያየ የኢትዮጵያ ክፍሎች መጭውን ትውልድ ባገናዘበ ሁኔታ እየተሳለጡ ነው።

በአፍሪካ መዲና በአንድነት እና የወዳጅነት ፓርኮች ጅማሮውን ያደረገው የዘርፉ ልማት፤ ወደ ወንጪ ኢኮቱሪዝም፣ ጎርጎራ፣ ሎጎ ሐይቅ ሪዞርት፣ የሸበሌ ሪዞርት፣ ሶፍዑመር ዋሻ፣ ባሌ ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ፣ የዝሆኖች ዳና ሎጂ፣ የኒዒን ሌ ፓልም ሎጂ ድረስ ወዘተ… ዘልቋል። እንደቀጠለም ነው።

እነዚህም ፀጋን ለይቶ ወደ ሃብት በመቀየር ሂደት በመንግሥት ብርታት የለሙ መዳረሻዎች ናቸው። መንግሥት ነባር መዳረሻዎችን በመጠገንና በማደሥ፤ አዳዲስ መዳረሻ በመገንባት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም አልሠሠተም፤ ብዙ እየሠጠ ነው።

✍️ ከቱሪዝም ዘርፍ አንጻር የሕብረተሰቡ ሚና

ቱሪዝም በተፈጥሮው ከበርካታ ጉዳዮች ጋር ይተሣሠራል። በእጅጉ ሰላም ይሻል፤ የሰላም ባለቤት ደግሞ ሕዝቡ ነው። ዘርፉ የቅርሶችንና መዳረሻዎችን ልማትና እንክብካቤም ይሻል። ለዘርፉ የሚሰጥ ትኩረት ሀገርንም፤ ሕዝብንም ይጠቅማል፤ ጥቅሙ ከዕለት ጉርስ እስከ ጥሪት ይዘልቃል።

በዚህ ሂደት ሕዝቡ በየአካባቢው ያሉ ብሔራዊ ፓርኮችን፣ ቅርሶችን እና የቱሪስት መዳረሻዎችን የኔ ብሎ መጠበቅ ይኖርበታል። ለምሳሌ፡- ብሔራዊ ፓርክ ወይም በመዳረሻ ላይ ጉዳት ቢደርስ በቀጥታ ተጎጂው የአካባቢው ነዋሪ ነው። ምክንያቱም ቱሪስት ካልሄደና ገቢ ካልተገኘ ገቢ ይደርቃልና።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በከተማው በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተስተዋለውን ክፍተት ለማረም በተሰራው ሥራ ለውጥ መጥቷል

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...

Apr 30, 2026

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀጣናዊ ዘላቂ ሰላምና እድገትን በምርምር ማገዝ አለባቸው

ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...

Apr 30, 2026

የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...

Apr 29, 2026

‎ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግ ርብርብ እየተደረገ ነው 

‎ሀዋሳ ፤ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡-ሀዋሳ ከተማን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ ከተማዋ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከተማ እንድትሆን ርብርብ እየተደረ...

Apr 20, 2026