🔇Unmute
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) ገለፁ።
የለውጡ መንግስት ለከተሞች እኩል የመልማት ዕድልን አስገኝቷል-የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች
በዲላ ከተማ "የመጋቢት ፍሬዎች ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል የለውጡን መንግሥት የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) በዚህ ጊዜ እንዳሉት በለውጡ አመታት በክልሉ ከፍተኛ የልማት እድገት ተመዝግቧል።
ለዚህም ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲ ትግበራና ለሰው ተኮር እድገት የተሰጠው ትኩረት የራሱ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰዋል።
በከተሞች ኮሪደር ልማትን ጨምሮ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያ እንዲሁም በገጠር በግብርና እና በማዕድን ዘርፎች እምርታ መታየቱን ለአብነት አንስተዋል።
እነዚህን የለውጥ ጉዟችንን ስነዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶችን በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉም ገልፀዋል።
የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዞኑ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት አርሶ አደሩ በአመት ሶስት ጊዜ እንዲያመርት በማድረግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ገበያ ተኮር ምርት በስፋት መመረቱን ጠቅሰዋል።

የብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፍ ትግበራ ግብርናውን በማዘን ከዞኑ በአማካይ ከ40 ሺህ ቶን በላይ የቡና ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ በሌሎች ዘርፎችም የገቢ አቅም ማሳደግ መቻሉን አንስተዋል።
የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከርም የብልጽግናን ጉዞ ለማስቀጠል እየተሠራ መሆኑንም ገልፀዋል።
ከተሞችን የለውጥ ማዕከል የማድረግ ሀገራዊ ጥረት በዲላ ከተማ በተጨባጭ እየታየ ነው ያሉት ደግሞ የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን ደምሴ (ዶ/ር) ናቸው።

ይህም የለውጡ መንግሥት ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እና ፖለቲካዊ ተሳትፎን ያረጋገጠ መሆኑን ነው ያነሱት።
ባለፉት የለውጥ አመታት ብቻ የከተማውን ነዋሪ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ከ 252 በላይ የልማት ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት መብቃታቸውን ተናግረዋል፡፡
እነዚህ የለውጥ ትሩፋቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የነዋሪው የነቃ ተሳትፎ እንዲጠናከርም ጥሪ አቅርበዋል።

ከድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል መምህርት ስመኝ ታደሰ በሰጡት አስተያየት የለውጥ ዓመታትን መዘከር ተጨባጭ እድገትን ማስቀጠል ነው ብለዋል።
የለውጡ መንግሥት ሀገር በችግር ውስጥ በነበረችበት ወቅት ወደ ስልጣን በመምጣት ኢትዮጵያን ያሻገረ መሆኑን ጠቅሰው አጋርነታቸውን ለማረጋገጥ በድጋፍ ሰልፉ መሳተፋቸውን ገልጸዋል፡፡
ሰመራ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ለህብረተሰቡ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
May 21, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...
Apr 30, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...
Apr 30, 2026
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...
Apr 29, 2026