የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ቀጣናዊ ደኅንነትን በማስጠበቅ ለጋራ ብልፅግና ወሳኝ ነው

Apr 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን በመጠበቅ ለቀጣናዊ ትስስርና የጋራ ብልፅግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ''የቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ቀጣና የባሕር አስተዳደር፤ አካታችነትና ትስስር ለጋራ ጥቅም'' በሚል መሪ ሃሳብ አራተኛውን ዓመታዊ የውይይት መድረክ እያካሄደ ይገኛል።


የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ሉዓላዊ መዳረሻ ጥያቄ ታሪካዊ፣ ሕጋዊና ስትራቴጂክ መሰረትና ቅቡልነት ያለው ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከባሕር በር መዳረሻዎቿ የተገለለችበት ኢ- ፍትሕዊ በደልም በቀጣናዊ ጂኦ - ፖለቲካዊ የኃይል ሚዛንና የባሕር ላይ ደኅንነት ጥበቃ የሚጠበቅባትን ገንቢ ሚና እንደገደበው አስረድተዋል።

የኢትዮጵያን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትና የህዝብ ቁጥር የልማት ፍላጎት ለማሳለጥም አስተማማኝ የባሕር በር ማግኘት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ጠንካራ የባሕር ኃይል ግንባታም የባሕር ላይ ውንብድና፣ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ሽብርተኝነትና መሰል ስጋቶችን ለመዋጋት ከፍተኛ የትብብር አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የቀይ ባሕርና ኤደን ባሕረ ሰላጤ ሉዓላዊ መዳረሻ ፍላጎትና ጥያቄም ዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደኅንነትን በማረጋገጥ ለቀጣናዊ ትስስርና የጋራ ብልፅግና የላቀ ፋይዳ እንዳለው አስገንዝበዋል።

የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ በበኩላቸው፤ የቀይ ባሕርና ኤደን ባሕረ ሰላጤን ዘላቂ ሰላምና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማሳለጥ ሁሉንም ሀገራት የሚያሳትፍ የባሕር ላይ አስተዳደር መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።


የኢትዮጵያ አስተማማኝ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም ቀጣናዊ ትስስርን በማጎልበት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የተመሰረተ መሆኑን አስረድተዋል።

ለዚህም የንግድ መዳረሻ ወደቦችን ኢኮኖሚያዊ አስተሳሳሪ ሰንሰለትነት የሚያገለግሉበትን ወሳኝ የውሃ ላይ የአስተዳደር ሥርዓት መፍጠር እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

በውይይቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ተጋባዥ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ ለህብረተሰቡ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ ነው-ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

ሰመራ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል ለህብረተሰቡ የዘመናት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጡ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት እየበቁ መሆናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

May 21, 2026

በከተማው በትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተስተዋለውን ክፍተት ለማረም በተሰራው ሥራ ለውጥ መጥቷል

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ ከነዳጅ እጥረት ጋር በተያያዘ በህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የነበረውን ክፍተት ለማረም...

Apr 30, 2026

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀጣናዊ ዘላቂ ሰላምና እድገትን በምርምር ማገዝ አለባቸው

ጅማ፤ ሚያዝያ 21/2018(ኢዜአ)፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የምርምር ሥራዎቻቸውን ከቀጣናዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ዘላቂ ሰላምና የጋራ እድገት ለ...

Apr 30, 2026

የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ ነው 

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦የትራንስፖርት አገልግሎትን ከነዳጅ ጥገኝነት ለማላቀቅ ተግባራዊ የተደረጉ ስልቶች ተጨባጭ ውጤት እያመጡ መሆኑን የትራን...

Apr 29, 2026