የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ለትንሣዔ በዓል የተሻለ የእርድ እንስሳትና የበዓል የፍጆታ ምርት አቅርቦት አለ-ሸማቾችና ነጋዴዎች

Apr 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በአዳማ ከተማ ለዘንድሮ የትንሣዔ በዓል የተሻለ የእርድ እንስሳትና ሌሎች የፍጆታ ዕቃ አቅርቦት መኖሩን ሸማቾችና ነጋዴዎች ገለጹ።

በአዳማ እሮብ የእንስሳት ገበያ ሲገበያዩ ካገኘናቸው ሸማቾች መካከል አቶ ፍቅሬ ለማ በሰጡት አስተያየት በከተማዋ ለትንሣዔ በዓል በቂ የእርድ እንስሳት መኖሩን ይገልጻሉ።

አንድ መካከለኛ ሠንጋ በ90 ሺህ ብር መግዛታቸውን የተናገሩት አቶ ፍቅሬ፤ ካለፈው የበዓል ገበያ ጋር ሲነጻጸር በደለቡ ሰንጋዎች ላይ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ የታየበት መሆኑን ነው ያስረዱት።


ሌላኛው ሸማች አቶ ተሾመ ቱፋ በበኩላቸው ለዘንድሮው የትንሣኤ ገበያ ካለፉት ዓመታት በተለየ መልኩ ሰፊ የእንስሳት አቅርቦት የታየበት ነው ብለዋል።


ዋጋውም ቢሆን ተመጣጣኝ ነው ያሉት አስተያየት ሰጪው፤ እሳቸው ከስደስት ጓደኞቻቸው ጋር አንድ መጠነኛ በሬ በ80 ሺህ ብር መግዛታቸውን ገልጸዋል።

ሌሎች ሸማቾችም የቁም እንስሳት ግብይት አቅርቦት በተሻለ ሁኔታ መኖሩን ጠቅሰው አንድ ሠንጋ በሬ እስከ 160 ሺህ ብር ጥሪ መኖሩን ተናግረዋል።

ከሠንጋ ነጋዴዎች መካከል አቶ ታደሰ ፈይሳ በበኩላቸው፤ ለበዓሉ በቂ አቅርቦት በመኖሩ ገበያው የተረጋጋ መሆኑን ተናግረዋል።


አሁን ላይ ያለው የእርድ እንስሳት ዋጋ ከባለፈው ገና በዓል ጋር ሲነጻጸር መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።

በአዳማ ቦሎ ገበያ ዶሮ እና እንቁላል ሲገበያዩ ያገኘናቸው አቶ ደበበ ፍቃዱ ለበዓሉ በቂ የዶሮ አቅርቦት እንዳለ ጠቅሰው እሳቸው ሁለት ዶሮዎችን መግዛታቸውን ተናግረዋል።


የዶሮ ነጋዴ አበራ መክቴ በበኩላቸው፤ ለበዓሉ በቂ አቅርቦት በመኖሩ ሁሉም ባለው አቅም መርጦ በመግዛት በዓሉን እንዲያከብር ያስችለዋል ብለዋል።

አሁን ላይ አንድ ዶሮ ከ 1 ሺህ 500 እስከ 2 ሺህ ብር ዋጋ መቅረቡን ጠቅሰው ይህም ዋጋ ካለፉት በዓላት ጋር ሲነጻጸር ተመጣጣኝ መሆኑን አስረድተዋል።

የአዳማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ከድጃ ጀማል፤ በከተማዋ የሚገኙ የእንስሳት ገበያዎች የበግ፣ የፍየል፣ እንዲሁም የቀንድ ከብት አቅርቦት የተሟላ እንዲሆን አስቀድሞ መሰራቱን ገልጸዋል።


ለእርድ እንስሳት ንግድ መሳለጥም አዲስ የእንስሳት ገበያ በቦሌ ክፍለ ከተማ ጎሮ ወረዳ መከፈቱን ጠቅሰው ህብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኙ ገበያዎች መጠቀም እንደሚችልም አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026