የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የሕብረት ሥራ ማህበራት በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

Apr 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሃዋሳ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦-የሕብረት ሥራ ማህበራት በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ለማሳደግ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ 2ኛውን ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ በተለያዩ ከተሞች በማካሄድ ላይ ይገኛል።


በሀዋሳ እየተካሄደ ባለው መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር)፤ ከተናጠል ጥረት በሕብረት በተደመረ አቅም የሚከናወኑ ተግባራት ለሀገል ልማትና እድገት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም መሰረት በለውጡ ዓመታት የሕብረት ሥራ ማህበራት በሀገር ልማትና የምጣኔ ሃብት እድገት ላይ የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል፤ በዚህም ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

ሕብረት ሥራ ማህበራት የአስተሳሰብ፣ የአደረጃጀት፣ የአሰራርና የአመራር ሪፎርም ካደረጉ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም በቀጣይ በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

የሕብረት ሥራ ማህበራት የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል ወሳኝ መሆናቸውን በማንሳት ቀጣይነት እንዲኖራቸው መሰል ንቅናቄዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል።


የፌዴራል ሕብረት ሥራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሺሰማ ገብረስላሴ፤ የሕብረት ሥራ ማህበራትን አቅም በማሳደግ ለሀገራዊ የብልጽግና ጉዞ የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም በሀዋሳ፣ አዳማ፣ ጅማ፣ ጅግጅጋ፣ አሶሳና ኮምቦልቻ ከተሞች በዛሬው እለት ተመሳሳይ መድረኮች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው በሌሎችም ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026