🔇Unmute
ጅማ፤ ሚያዝያ 13/2018(ኢዜአ)፦ ህብረት ስራ ማህበራት የተሻለ ቁመና ላይ እንዲደርሱ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት እየመጣ መሆኑን የኢትዮጵያ የህብረት ስራ ኮሚሽን ገለጸ።
ሁለተኛው ዙር "ቀበሌ የመድረስ ምዕራፍ" ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ሪፎርም ንቅናቄ በዛሬው ዕለት በስድስት ክላስተሮች መሰጠት ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን የህብረት ስራ ኦዲት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ጠሀ ዲጋ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት ዘመናዊ መሆንና መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት ለሀገር ኢኮኖሚ ጠንካራ መሠረት ነው።
ቀደም ሲል የማህበራቱ አደረጃጀት በፅኑ መሠረት ላይ ባለመሆኑ ቀጣይነታቸው ጥያቄ ውስጥ ሲገባ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን እየተተገበረ ባለው ሪፎርም ተስፋ ሰጪ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ መድረክ በዋናነት በማህበራቱ አመራርና ባለሙያዎች ዘንድ የአመለካከትና የእውቀት ለውጥ ለማምጣት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የጅማ ዞን የህብረት ስራ ማህበራት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ድማሙ ንጋቱ በበኩላቸው፤ የህብረት ስራ ማህበራት የሀገሪቱን የልማት ጉዞ በማፋጠን ረገድ ያላቸው ሚና የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም የፋይናንስ ተቋማት ተሳትፎ እየጨመረ መምጣቱ ለማህበራቱ መጠናከር ትልቅ ድርሻ ማበርከቱን ገልጸዋል።
በጅማ ከተማ እየተካሄደ ባለው በዚህ ንቅናቄ ከጋምቤላ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ከኦሮሚያ ክልሎች የተውጣጡ 400 የህብረት ስራ ማህበራት የልማት ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026