የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በጎንደር ከተማ ገጠር ቀበሌዎች ለ100 ሺህ የእርሻ መሬት ባለይዞታዎች ዲጂታል ካርታ እና የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ሊሰጥ ነው

Apr 30, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጎንደር፤ ሚያዝያ 21/2018 (ኢዜአ)፦ በጎንደር ከተማ አስተዳደር በገጠር ቀበሌዎች ለ100 ሺህ የእርሻ መሬት ባለይዞታዎችዲጂታል ካርታ እና የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ መሬት መምሪያ አስታወቀ፡፡

በከተማው ገጠር ቀበሌዎች ለመሬት ባለይዞታዎች የማረጋገጫ ደብተር ለመስጠት የካዳስተር ሥራ ማስጀመር የሚያስችል የአጋር አካላት የምክክር መድረክ ዛሬ ተካሂዷል፡፡


የመምሪያው ምክትል ሃላፊ አዛናው መልካሙ በመድረኩ እንደገለጹት፤ ዘመናዊ የዲጂታል የመሬት ምዝገባ ስርአት የአርሶ አደሩን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በዘላቂነት የሚፈታ ነው፡፡

በከተማው በታቀፉ 11 የገጠር ቀበሌዎች ለ100 ሺህ የእርሻ መሬት ባለይዞታዎች2ኛ ደረጃ ዲጂታል ካርታና የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለመስጠት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም 1ሺህ 283 ባለይዞታዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸው፣ ማረጋገጫው መሰጠቱ አርሶ አደሩ ህጋዊ የመሬት ባለቤትነቱን በማረጋገጥ መሬቱን ለመንከባከብና ለማልማት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

በተጨማሪም የማረጋገጫ ካርታውን አስይዞ ከአበዳሪ ተቋማት የገንዘብ ብድር እንዲያገኝ ዋስትና እንደሚሰጠው ገልጸው፣ በመሬት ይገባኛል የሚነሱ ግጭቶችን እንደሚያስወግድም አስረድተዋል።

ዲጂታል የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ደብተር የመስጠት ሥራውን በተያዘው የሚያዚያ ወር መጨረሻ በማስጀመር እስከ ቀጣዩ ዓመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ተወካይ መኮንን ተሾመ በበኩላቸው፤ መሬት ትልቅ ሀብት በመሆኑ መረጃውን በሳይንሳዊ መንገድ ሰንዶ ለሚፈለገው ልማት ማዋል ይገባል ብለዋል።

በጎንደር ከተማ የአንቸው ገጠር ቀበሌ ነዋሪ ሴት አርሶ አደር ተዘሩ አለማየሁ፤ ከዚህ በፊት የተሰጣቸው የመጀመሪያ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ከባንክ ብድር አውጥተው በልማት ስራ ለመሰማራት እንቅፋት እንደሆነባቸው አስታውሰዋል።


አዲሱ ዲጂታል የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ከባንክ ለመበደር ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸው፣ ካርታውን ለማግኘት አስፈላጊውን የባለቤትነት ማስረጃዎች አደራጅቼ እየጠበኩ ነው ብለዋል።

ዲጂታል የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የመሬት ወረራን ለማስቀረት ትልቅ ፋይዳ አለው ያሉት ደግሞ በከተማ አስተዳደሩ የሳቢያ ሳይና ገጠር ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር እያዩ አሊ ናቸው፡፡


በምክክር መድረኩ ከገጠር ቀበሌዎች የተውጣጡ አርሶ አደሮች፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026

በዞኑ የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ አጠናቆ ወደ ስራ ለማሰገባት አስችሏል

አምቦ፤ሐምሌ 16/2018(ኢዜአ)፡- በምዕራብ ሸዋ ዞን የሰፈነው ስላም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ እን...

Jul 24, 2026

 በዞኑ እየተካሔደ ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጎንደር፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ጎንደር ዞን የተጀመሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የዞኑ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ...

Jul 23, 2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪ ኤክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8/2018 ( አዜአ) ፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአፍሪ ኤክሲም ባንክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ኤሎምቢ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል።...

Jul 16, 2026