🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የተገነቡ ግዙፍ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ሕይወት እያሻሻሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ ሱቆችናየህጻናት መጫወቻ ፓርኮችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ከንቲባዋ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፓስተር አካባቢ የተገነባ ባለአምስት ወለል የመኖሪያ ቤት ህንጻን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች አስረክበዋል።
እንዲሁም በክፍለ ከተማው 40/60 ብርጭቆ ኮንደሚኒየም አካባቢ የተገነቡ ሁለገብ የህዝብ መዝናኛ ፓርክን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት፤ አዲስ አበባ ከስም በዘለለ በተግባር ውብ እና አበባ እየሆነች ትገኛለች ብለዋል።
በከተማዋ የተገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተመራጭ ከተማ እንድትሆን እንዳስቻሏት ገልጸዋል።

የከተማዋ ልማት ከዜጎች ህይወት መለወጥ እና መዘመን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው መሆኑን አመላክተዋል።
በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ፣ ምቹ የመኖሪያና የመዝናኛ አማራጭ የሚፈጥሩ እና የቱሪስት መስህብ መሆን የሚችሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ነዋሪዎች የተገነቡትን ውብ የልማት ፕሮጀክቶች በአግባቡ በመጠበቅና በመንከባከብ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው የልማት ፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው፤ የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶች፣ የህፃናት መጫወቻ ፓርኮች ወደ ዘመናዊና ምቹ አኗኗር የሚያሸጋግሩ ናቸው ብለዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026