🔇Unmute
ጋምቤላ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦የጋምቤላ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በአንድ ዙር 57 ሺህ ጫጩቶችን ማስፈልፈል የሚያስችል የዶሮ ምርምርና ብዜት ማዕከል በማስገንባት ላይ መሆኑን አስታወቀ።
ኢንስቲትዩቱ በጋምቤላ ከተማ ከ58 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ እያካሄደ ያለውን የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ሂደቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ዓለሚቱ ኡሞድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ጎብኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሯ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ማዕከሉ የዶሮ እርባታውን ለማዘመንና ለማስፋት ዓይነተኛ ሚና ይኖረዋል።

በተለይም እንደ ሀገር ጤናማ የአመጋገብ ስርዓትን ለማጠናከር እየተተገበረ ያለውን የሌማት ትሩፋት መርሃግብር ስኬታማ ለማድረግ የጎላ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በመሆኑም የግንባታውን ሂደት በማፋጠን ወደ ስራ ለማስገባት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ለማዕከሉ ግንባታ መፋጠን የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋልም ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሯ።
የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሪያል ጂንግ፤ ኢንስቲትዩቱ በምርምር የተሻሻሉ የእንስሳትና የዕጽዋት ዝርያዎችን በማውጣት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

ኢንስቲትዩቱ እያስገነባ ያለው የዶሮ ምርምርና ብዜት ማዕከል የተሻሻሉ ዝርያዎች ለአርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች ተደራሽ ለማድረግ ያለም መሆኑንም ተናግረዋል።
በምርምር ኢንስቲትዩቱ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አብዮት አለማየሁ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ የማዕከሉ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ በአንድ ዙር 57 ሺህ ጫጩቶችን የማስፈልፈል አቅም አለው።
በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ ከ58 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለው ማዕከሉ አሁን ላይ ግንባታው ከ80 ከመቶ በላይ መድረሱን ገልጸዋል።
የማዕከሉን 2ኛ ምዕራፍ ግንባታንም ለማስጀመር የጨረታ ሂደቱ መጠናቀቁንና በቅርቡ ስራው እንደሚጀመር አቶ አብዮት ገልጸዋል።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026