🔇Unmute
ጋምቤላ፤ ግንቦት 30/2018 (ኢዜአ)፡- የአረንጓዴ ዐሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብሮች የፈጠሩትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስኬታማ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የጋምቤላ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ አንድሮው ቱት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ሐባብና ብርቱካንን ጨምሮ ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎች በአርሶ አደሮችና ባለሃብቶች በስፋት እየተመረቱ ነው።
በተለይም በጎደሬና በመንጌሽ ወረዳዎች አቮካዶና ሙዝን ጨምሮ ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ወደ አዲስ አበባና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ለገበያ በስፋት እየቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል።
በዘንድሮው ክረምትም ከአረንጓዴ ዐሻራ ልማቱ ጋር በማቀናጀት አቮካዶን ጨምሮ ከ8 ሚሊየን በላይ የፍራፍሬና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።

የጎደሬ ወረዳ ጌለሻ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ሉቃስ ጎርሾ፤ ሙዝ፣ አቮካዶና ሌሎችንም የሰብል እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬዎች በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት በሙዝ ልማት በስፋት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆኑን የገለጸው ደግሞ የዚሁ ቀበሌ ነዋር ወጣት ሮቤል ሮኬት ነው።

በአሁኑ ወቅት በሰባት ሔክታር ላይ ሙዝ በማልማት ምርቱን በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች በመሸጥ ተጠቃሚ መሆኑን ነው ያረጋገጠው።
አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...
Sep 11, 2026
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...
Aug 31, 2026
ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...
Aug 17, 2026
ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...
Jul 27, 2026