የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በሐረሪ ክልል ከገጠር ኮሪደር ልማት ጋር የተሳሰሩ አዳዲስ የገጠር መንገዶች ግንባታ እየተከናወነ ነው

Jun 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረር፤ ሰኔ 2/2018 (ኢዜአ) ፡-በሐረሪ ክልል ከገጠር ኮሪደር ልማት ጋር የተሳሰሩ አዳዲስ የገጠር መንገዶችን የመገንባት ሥራ በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በሀገሪቱ ከተሞች የተጀመረውና ውጤታማነቱ የተመሰከረለት የኮሪደር ልማት ንቅናቄ፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ገጠር አካባቢዎች በመስፋፋት ላይ ይገኛል።

የሐረሪ ክልልም ይህንን ሀገራዊ ራዕይ ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የከተማና የገጠር ትስስርን ለማጠናከር በትኩረት እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኢንጅነር ፈቲህ ተውፊቅ እንዳሉት፤ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በገጠር የመንገድ ተደራሽነትን ለማጎልበት መጠነ ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል።

የጠጠር መንገድ ግንባታ ሥራዎቹም ለአርሶ አደሩ በበጋና በክረምት ምርቱን ወደ ገበያ እንዲያቀርብ በማድረግና ሌሎች አገልግሎት በመስጠት ተጠቃሚነትን እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል።


ዘንድሮም በተለያዩ ፕሮግራሞች የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማጎልበት የከተማና ገጠር ትስስርን የማጠናከር እና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በክልሉ ሶስት ወረዳዎች በመደበኛ በጀትና በገጠር መንገድ ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም 77 ኪሎ ሜትር አዳዲስ የገጠር መንገድ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም በካፒታል ፕሮጀክት 54 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን አዳዲስ የገጠር መንገዶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፤ ቀሪው 23 ኪሎ ሜትር ግንባታ ደግሞ በገጠር መንገድ ትስስር ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም አማካኝነት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ከገጠር ኮሪደር ልማት ጋር በማስተሳሰር እየተካሄደ ያለው አዳዲስ የገጠር ጠጠር መንገዶች ግንባታን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አዳዲስ የጠጠር መንገድ ግንባታዎቹ በህዝቡ ዘንድ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ ከመሆናቸው ባለፈ ከገጠር ኮሪደር ልማት ጋር የተሳሳሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የመንገዶቹ መገንባትም ቀበሌዎችን እርስ በእርስና ከከተማው ጋር የሚያገናኝ መሆኑን ጠቁመው በዚህም በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ችግር ከመሠረቱ የሚቀርፍ መሆናቸውን አመልክተዋል።

በከተማው ውስጥ አዳዲስ የአስፋልትና የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ፣ የጥገና፣ ደረጃዎችን የማሻሻልና ሌሎች ስራዎችን የማከናወን ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አክለዋል።

በሐረሪ ክልል በሁለተኛው ዙር ሞዴል የአርሶ አደሮች መንደር ፕሮጀክት 250 ቤቶች የመገንባት ስራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026